እንኳን ወደ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በደህና መጡ!
የሀሳብ_ልዕልና_ለሁለንተናዊ_ብልጽግና !!
እንኳን ወደ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በደህና መጡ!
እንኳን ደስ አላቹሁ !
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከሚገኙ ከ11ዱም ወረዳዎች መካከል 2ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ እና ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ ተማም ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት ይህንን ውጤት እንዲመጣ ከጎናችን ሆናቹ የላቀ ሚና ለተወጣቹ የወረዳችን አስተባባሪ ኮሚቴ፣ አጠቃላይ አመራሮች፣ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 27 ቀን 2017
ወደ ተምሳሌት ሀገር በተሻገረ ህልም በላቀ የአባላት ትጋት አስተማማኝ ነገን መስራት!!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ " ወደ ተምሳሌት ሀገር በተሻገረ ህልም በላቀ የአባላት ትጋት አስተማማኝ ነገን መስራት!! " በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ በደመቀ መልኩ አካሄዷል::
ብልጽግና እንደ ፓርቲ ከተመሰረተበትና የህዝብን ይሁንታ ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ሰው ተኮርና ታላላቅ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሪፎርሞችን በማድረግ ዕምርታዎችን አስመዝግቦ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያመላክቱ ተግባራትን አከናውኗል። ፓርቲው በምርጫ ለህዝቡ የገባውን ቃል በማክበር ዘርፈ ብዙ ለውጦችን በማምጣት እየሰራ ሲሆን በቀጣይም ተጨማሪ ድሎችን ለማሳካት ከመላ አባላቱ ጋር በየደረጃው አካሄዷል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ ሚካኤል በመክፈቻ ንግግራቸው የዛሬው ኮንፈረስ በክፍለ ከተማው ባለፈው በጀት ዓመት የተመዘገበውን የላቀ ውጤት ለማስቀጠልና የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነትና ተሳትፍ ለማጠናከር እንዲሁም ነዋሪውን በቁርጠኝነት እና ተአማኒኑት ለማገልገል የአባላት ግንባር ቀደም ተሳትፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የአባላት አቅም ግንባታን በማሳደግ የፓርቲያችንን የለውጥ ቱርፋት የሰው ተኮር ስራዎችን ማጠናከር ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣ የአካባቢን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣ አባላትን በጥራት መልሶ ማደራጀት፣ ለምርጫ ስራዎች ቅድመ ዝግጅት የማድረግ ተግባራት በቤተሰብ እና በህብረት ደረጃ በትኩረት ማከናወን እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አሚ ሙሄ በበኩላቸው የ2018 በጀት አመት የዝግጅት ምዕራፍ 1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ መካሄዱ በቀጣይ ተግባር ምዕራፍ ይበልጥ ጠንክረን በመስራት ውጤት ለማስመዝገብ የሚያነሳሳና ጠንካራ የፓርቲ ተቋማት ጠንካራ የፓርቲ አባል ለማብቃት የሚያዘጋጅ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ። ይህም የሚሆነው በመደመር እሳቤ በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ በጋራ መስተጋብር በመፍጠር ለተሻለ ውጤት የሚያዘጋጅ ፣ በጥራትና በብዛት ጠንካራ ተቋምና አደረጃጃት የሚፈጥር መሆኑንም ገልጿዋል።
ፓርቲያችን ብልፅግና የጀመራቸውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጃት ያለው አባል ያስፈልጋል ይህ ደግሞ የዛሬው የኮንፈረስ መድረክ ይበልጥ ያዘጋጃል ያነቃቃል ፤ ስለሆነም አባላት በፓርቲ አደረጃጅት በመጠርነፍ የፓርቲውን ተልዕኮ ወስዶ በብቃት በጋራ ሆነን መፈፃም ያስፈልጋልም ብለዋል።
በኮንፈረሱም የፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት እቅድ እና የ1ኛ ሩብ አመት የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች አፈፃፀም እንዲሁም የክፍለ ከተማው የኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽ የ2018 እቅድ እና የ2017 ዓ.ም የኢንፔክሽን ግኝት ቀርበው ውይይት ተካሄዶበታል።
በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ በየወረዳው ያሉ ህብረቶች እና ዘርፎች እና ለወረዳዎች እውቅና ተሰጥቷል።
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
“ዓባይን ጨርሶ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሪክ እጥፋትን ማረጋገጥ የመጨረሻው ጸሎቴ፤ የመጨረሻው ምኞቴ ነበር”
:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
እንኳን ደስ አላችሁ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከክፍለ ከተማው ከ11ዱም ወረዳዎች በስራ አፈፃፀም ተመዝኖ 1ኛ ወጣ!! ተቆጥረው በተሰጡት ዓበይት ተግባራት አንፃር ስራዎች ተመዝኖ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በማግኘት የእውቅና ሰርተፊኬት፣ ላፕቶፕና ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል
በተጨማሪ በ3ቱም ቡድን
ከቁጥጥር ቡድን 1ኛ
ከቅድመ መከላከል ቡድን 1ኛ
ከፋይናንስ ቡድን 1ኛ
ከባለሙያዎች አጠቃላይ ከ11ዱም ወረዳ 1ኛ በመውጣት ለሁሉም የአምስት አምሰት ሺ የህዳሴ ቦንድ እና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖል ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ትልቁን እገዛ ላደረጉ የወረዳ አስተባበሪ ኮሚቴ፣ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 25 ቀን 2017
ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ወደ ተምሳሌት ሀገር በተሻገረ ህልም ፣ በላቀ ትጋት ፣ አስተማማኝ ነገን መስራት!
በዛሬ ዕለትም ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት በወረዳ ደረጃ የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ በድምቀት ተካሄደ።
በመርሀግብሩም የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሰው ሀይል እና የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉ ደስታ፣ የወረዳችን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ፣ የወረዳችን ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ከበደ ጥላሁን፣ የወረዳችን ብልጽግና ኢንስፔክሽን ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ወ/ሮ ነዒማ አህመድ፣ የወረዳ አመራሮች የፓርቲያችን አባላት ታድሞዎል።
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ አመታት በርካታ ስራዎችን በመስራት ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር ቀይሮ ያሳየ በህዝቡም ዘንድ ትልቅ አመኔታ ያተረፈ ውጤታማ ፓርቲ ነው።
ባለፉት ሳባት የለውጥ አመታት ብልጽግና ፓርቲ ሀገሪቱ ከነበረችበት የኢኮኖሚ፣ የፓለቲካ፣ የማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ አዙሪት ወጥታ ከተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገራት ተርታ መሰለፍ እንድትችል ብልጽግና በሳልና ቆራጥ አመራር ሰጭነት እጅግ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
የፓርቲያችን ብልጽግና አባላት ከፓርቲው እሳቤ ጋር በመሆን በወጀብ ሳይናጡ በቁርጠኝነት በመጓዝ ፓርቲው ላስመዘገበው ውጤት ሚናቸውን በሚገባ እየተወጡ ይገኛሉ።
የ2018 በጀት አመት የፓርቲ እቅድ አፈፃፀም ፣ የቀጣይ እቅድ እና የትኩረት አቅጣጫ በወረዳችን ብልጽግና ፓርቲ ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ ተማም በተመሳሳይ በወረዳዉ ኢንስፔክሽን ስነ ምግባር ኮሚሽን የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ፣ እቅድ ወ/ሮ ነዒማ አህመድ ሰነዶች ቀርቦ በሰፊዉ ውይይት ተካሂዷል።
በመርሀግብሩም የተሰሩ መልካም ተሞክሮዎች፣ የታዩ ክፍተቶች በፍጥነት በማረም የምናልመዉ ሀገር በአባላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ በተግባር ለማረጋገጥ በትጋት መስራት እንደ ሚገባ ተገልፁዋል።
በመጨረሻም በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄደዉ የማጠቃለያ ኮንፍረንስ ምርጫ እና በተጎደሉ የኢንስፔክሽን ስነ ምግባር ኮሚሽን አመራሮች ላይ የመተካት መርሀግብር በማካሄድ ተጠናቋል።
ነሀሴ 25 ቀን 2017
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረስ
ሳምንታዊ የፓርቲ ስራዎች ተገመገመ
ፓርቲን ለማጠናከር ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ ነው። አቶ ሚሊዮን ወንድሙ
የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ኮሚቴ የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ክፍተቶችና ጥንካሬዎችን በማንሳት እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸውን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ግምገማ አድርገዋል።
የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ የተገመገሙ ሲሆን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ ፓርቲን ለማጠናከር ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ መሆኑ ገለፀው ጥንካሬያችንና ድክመቶችን ለይተን ተግባርቶቻችን ላይ በጋራ ተረባርበን ሁሉም ለተመደበበት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የተሻለ ውጤት ማምጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ፤
የደም ጠብታ
የላብ ጠብታ
የዕንባ ጠብታ
የውኃ ጠብታ
ድምር ውጤት መሆኑን፣ ይህ ግድብ ህያው ምልክት ሆኖ ለትውልድ ሲመሰክር ይኖራል።
:- ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ
የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ
የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ
የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ
የአይበገሬነታችን ማሳያ፣ የሀገራችን ትንሳኤ ማብሰሪያ ግድብ!
ኢትዮጵያዊያን በጋራ ጉዳያቸው ላይ በህብር ደምቀው ከመሪዎቻቸው ጎን በመቆም የቁጭት ምንጭ ሆኖ በቆየው በዓባይ ወንዝ ላይ አኩሪ ታሪክ ፅፈዋል፡፡ በቅርቡ ለምርቃት የሚበቃው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትብብራችን ውጤት ነው፡፡ ተጋርጠውበት የነበሩትን በርካታ ተግዳሮቶች እንዲሁም ጫናዎች በድል አድራጊነት በመሻገር ለፍፃሜ የበቃው ግድባችን አይበገሬነታችንን ለዓለም አሳይቷል፡፡
የሰንደቅ ዓላማችን ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድባችን የተለያዩ ሴራዎችን በመበጣጠስ፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ ጫናዎችን በመቋቋም በእልህ እና ወኔ በማለፍ ለፍሬ ያበቃነው አንደኛው የብሔራዊ ኩራታችን ምንጭ ነው፡፡ በአድዋ ጦርነት በወራሪዎች ላይ የተረባረበው የኢትዮጵያውያን ክንድ በዘመናችንም የጣና ሀይቅን ሁለት እጥፍ የሚያህል የውሀ መጠን የሚይዝ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ግዙፍ ግድብ ገንብቷል፡፡
የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በላብአችን የፃፍነው፣ በድካማችን ያሳካነው አኩሪ ታሪካችን ጭምር ነው። በቅርቡ ሪቫን የምንቆርጥለት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ትስስራችንን ይበልጥ በማጥበቅ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያበስራል።
ኑ_እንሸምት
ነሀሴ 17/2017ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ የሠንበት ገበያና መገኛ ቦታዎቻቸው 16ቱም የሠንበት ገበያ ማዕከላት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘው ለሸማቾች ጥሪያቸውን አቅርበዋል!! ዋጋችን ተመጣጣኝ፣ አቅርቦታችን ፈጣን ነው። ኑና ሸምቱ ብለዋል።
"አዲስ አበባን ለእንግዶቿ እና ለነዋሪዎቿ ጽዱና ንፁህ እናደርጋታለን!" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ አስመልክቶ ከተማዋን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ምቹና ፅዱ ለማድረግ የሚያስችል የጽዳት ንቅናቄ ዘመቻ ተካሄደ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ጽዳትና ውበት ጽ/ቤት በዛሬው እለት "አዲስ አበባን ለእንግዶቿ እና ለነዋሪዎቿ ጽዱና ንፁህ እናደርጋታለን!" በሚል መሪ ቃል
የወረዳ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቆያ ላሌ እንዲሁም በየ ደረጃ የሚገኙ የወረዳና የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች፣ ነዋሪዎች፣ ደንብ ኦፊሰሮች፣ ባለሙያዎች፣ የጽዳት ማህበራትና ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች በተገኙበት የጽዳት ንቅናቄ ዘመቻ ተካሄደ
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቆያ ላሌ እንደገለጹት ግቢያችን፣ አካባቢያችን ብሎም ከተማችን በማጽዳት አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ ማራኪና ለነዋሪዎቿ፣ ለኑሮ የተመቸች ማድረግ አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፏል።
አቶ ለማ ቱሉ የኮልፌ ቀራንዮ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት ጽዳት የውበትና የስልጣኔ መገለጫ ነው፣ ጽዳት የሁላችንም ጉዳይ ሲሆን ነዋሪው ህብረተሰብ አካባቢውን በማጽዳት አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ ማራኪና ለኑሮ ተመራጭ አካባቢ መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።
ነሀሴ 17/2017 ዓ.ም
ጽዳት የውበትና የስልጣኔ መገለጫ ነው
ጽዳት የውበትና የስልጣኔ መገለጫ ነው
ጽዳት የውበትና የስልጣኔ መገለጫ ነው
ጽዳት የውበትና የስልጣኔ መገለጫ ነው
የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ ትምህርት ለትውልድ፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎች፣ የጽዳት ዘመቻ፣ የሰላምና ፀጥታ ስራዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የውስጠ ፓርቲ ስራዎችና ሌሎችም ተግባራቶች አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት የተሰሩ ስራዎች በመገምገም በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ላይ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
አቶ ለማ ቱሉ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት በተለይም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራትና ተግባራቶች አስተሳስሮ በመስራት ውጤታማነት ለማረጋገጥ ሁሉም አመራር፣ ፈጻሚውና አደረጃጀቱ ሚናው በበላይነትና በስኬት ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 16 ቀን 2017
በክፍለ ከተማው በ90 ቀን እቅድ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ግምገማ ተካሔደ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የክፍለ ከተማና የወረዳ ጠቅላላ አመራሮች በተገኙበት የ90 ቀን እቅድ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት በስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በበጎ ፍቃድ ተግባራት ፣ በሌማት ትሩፋትና በትምህርት ለትውልድ እንዲሁም በ90 ቀን እቅድ የተያዙ ዋና ዋና ግቦች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በዛሬው እለት ውይይት ተካሒዶበታል።
አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ በግምገማው ወቅት እንደገለፁት በ90 ቀናት በእቅድ ተይዘው የተፈፀሙ ተግባራት እንዳሉ ሆነው በሪፖርቱ የተመላከቱ የአፈጻጸም ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ህዝቡን የሚያማርሩ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ከስራ እድል ፈጠራ፤የአቅመ ደካማ የቤት እድሳት፤የውስጥ ለውሥጥ የመንገድ መብራት ማስወጣት እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ በ90 ቀን ተይዘው እየተከወኑ ያሉ ስራዎችን በፍጥነት አፈጻማቸውን ማሻሻል እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችንም በትኩረት መፈጸም እንደሚገባም አቶ ቴዎድሮስ አሳስበዋል፡፡ አቶ አሚ ሙሄ አሊ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው በ90 ቀን የተያዙ እቅዶችን አመራሩ ውጤት በሚያመጣ መልኩ በመምራት በውጤት መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
አቶ አሚ አያይዘውም ተግባራትን በውጤት ለመፈጸምና ለማሳካት መትጋት ርብርብ ማድረግ አስፈለጊ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስርአት መኖር እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ አቶ ኢብራሂም መሀመድ የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንደገለፁት የ90 ቀን እቅድ በበለጠ አፈፃፀም በተሻለ ተነሳሽነት አፈጻፀሙን ለማሳደግ መስራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ በቀጣይ የሚሰሩ ተግባራት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በክፍለ ከተማው በ90 ቀን እቅድ
በክፍለ ከተማው በ90 ቀን እቅድ
በክፍለ ከተማው በ90 ቀን እቅድ
በክፍለ ከተማው በ90 ቀን እቅድ
አዲስ አበባ ፡ በፈጣን የለውጥ እና የዕድገት ጎዳና !
የህዝባችንን ሲከማቹ የመጡ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በጥልቀት በመረዳት እልባት ለመስጠት ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙት ፕሮጀክቶቻችን ዘመን ተሻጋሪ እና ሰው ተኮር ናቸው። በጥልቅ ጉስቁልና ውስጥ በቆየችው ከተማችን አዲስ አበባ በመፍጠር እና በመፍጠን እየተሰሩ የሚገኙ ልማቶች የከተማችንን ተወዳዳሪነት ከፍ በማድረግ የህዝባችንን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ይገኛሉ። በሁሉም ክ/ከተሞች እና ወረዳዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ የሚገኙ ፕሮጀክቶቻችን የህዝባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት አሳድገዋል።
ህዝባችን በተደጋጋሚ ሲያነሳቸው የቆዩትን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በመመለስ የህዝባችንን እርካታ ከፍ ለማድረግ የሚደረገው ርብርብ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የከተማችንን የትራንስፖርት ችግር በመሰረታዊነት ለመፍታት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል የመኪና ማቆሚያዎችን በየአካባቢው ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ተሰርቷል ፤ እየተሰራም ነው፡፡ በግዙፉ አፍሪካዊ ተቋም በአፍሪካ ህብረት በቅርብ ርቀት ላይ የተገነቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የመኪና ማቆሚያዎች ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውም ትራንስፖርትን ከማሳለጥ የተሻገር ፋይዳ አላቸው።
የህዝባችንን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያቃለሉ የሚገኙት ፕሮጀክቶቻችን የከተማችንን ገፅታም በእጅጉ እየቀየሩ በመሆኑ በጉስቁልናዋ የምንሸማቀቅባት ሳይሆን በፈጣን ዕድገቷ የምንኮራባት ውብ ከተማ ሆናለች። አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የጀመርነው ብርቱ ጥረት አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቷን እና ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን እያሳደገ ይገኛል። ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የምትመች ፣ በጎብኝዎቿ የምትመረጥ ውብ ከተማ ለመገንባት እየተደረገ በሚገኘው ጥረት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሀዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልማቶች ሊስፋፉ ችለዋል። አዲስ አበባን ህፃናት በምቾት የሚያድጉባት አፍሪካዊት መዲና ለማድረግ የተጀማመሩ ጥረቶችም ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን በተለይም የህፃናት መዋያዎች እና መጫዎቻዎች በስራ እና በመኖሪያ አካባቢዎች ተደራሽ እየሆኑ ይገኛሉ።
የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን ከተደረጉ የአሰራር ማሻሻያዎች በተጨማሪ በየአካባቢው በመንግስት እንዲሁም በግሉ ዘርፍ እየተገነቡ የሚገኙ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላትም የከተማችንን ተወዳዳሪነት ከፍ አድርገዋል። በከተማችን ተጠናክሮ የቀጠለው ፈጣን የብልፅግና ጉዞ ሌሎችንም የሀገራችንን ከተሞች እያነቃቃ ሲሆን ፤ አዲስ አበባ ለሌሎች ሀገራትም ልምድና ተሞክሮዋን ለማካፈልም ጭምር ተመራጭ እና ተደማጭ ሆናለች። በርካታ ውስብስብ ችግሮችን በማስወገድ የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል አበረታች ስኬቶች ቢመዘገቡም መድረስ ከሚገባን እና ከህዝባችን አዳጊ ፍላጎቶች አንፃር ብዙ ስለሚቀረን ቅንጅታዊ ርብርቡን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል።
አዲስ አበባ እንደ ስሟ እያበበች ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ለጐብኚዎቿ ሳቢ ሆናለች።
:-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ አራቱ የመደመር ቅጾች ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያሰናዱት አራተኛው ቅጽ የመደመር መንግሥት መጽሐፍ በቀረበበት አግባብ ልክ በሀገርም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ፈር ቀዳጅ መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት መጽሐፍን አስመልክቶ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ስለ አራቱም ቅጾች ገለጻ አድርገዋል። በገለጻቸውም ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-
የመጀመሪያው ቅጽ መደመር የሚለው መጽሐፍ፤ ለመደመር አጠቃላይ እሳቤ መሠረት የሚጥል ነው። የመደመር ጽንሰ ሐሳብ ንድፈ ሐሳባዊ መሠረቱ የተቀመጠው በመጀመሪያው ቅጽ ላይ ነው። የመጀመሪያው ቅጽ ከሚያነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መካከል፤ የሰው ልጅ ፍላጎት ምን ይመስላል፣ ፍላጎቱን ለማሟላት በምን መንገድ ነው ሊራመድ የሚገባው የሚሉት ይጠቀሳሉ። እነዚህን ከሰው ጋር በማስተሳሰር መጽሐፉ በዝርዝር ያነሳል። በተጨማሪም ራሱ መደመር እንደ እሳቤ ምን ማለት ነው? የሚለውን በብዙ መገለጫዎች ያመላክታል።
መደመር ዓለምን እንዴት ይመለከታል? ስለ ዓለም ያለው ምልከታ በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው እና በዲፕሎማሲው ረገድ ምን ይመስላል? የሚለውም በመጀመሪዯው ቅጽ በዝርዝር አለ። በአጠቃላይ ቅጽ አንድ (መደመር) ሀገራዊ ጉዳዮቹን በፍልስፍና መነጽር ያስቀመጠ ሐሳብ ነው። ፍልስፍናዊ በሆነ መንገድ ያሉትን ችግሮች የሚተነትን ለእነዚያ ችግሮችም መልስ የሚያመላክት ነው። እንደ መደመር ያለ እሳቤ ለኢትዮጵያ አስፈላጊነቱ ምን እንደሆነም በዝርዝር አንስቷል።
ሁለተኛው ቅጽ የሆነው የመደመር መንገድ የተነሱትን ጉዳዮች ደግሞ ሐሳብ፣ ታሪክ፣ ስትራቴጂ በሚሉ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ከፍሎ ማየት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። በመደመር መንገድ ለይተን ካስቀመጥናቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አንዱ በወቅቱ የገጠሙንን ችግሮች በአራት የከፈልንበት ነው። እነሱም የለውጡ ሂደት የመደፈቅ አደጋ ያጋጠመበት፣ የለውጡን ሂደት ጥገናዊ ማድረግ፣ ለውጡን የተቀበሉ በመምሰል ለመጥለፍ የሞከሩ እና ለውጡ ሐቀኛ ሆኖ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ ማስቻል የሚሉት ናቸው። በለውጡ ጊዜ የተከተልነውን መንገድ ሊቀለብሱ (ሊጠልፉ፣ ተሃድሷዊ በሆነ መንገድ ሊያስኬዱ) የሚፈልጉ ኃይሎች እንዳሉ ገብቶን፤ ሊከተሉን በማይችሉት ፍጥነት ብንጓዝ አቅም እያነሳቸው እየተንጠባጠቡ ይሄዳሉ በሚል ይህን ሐሳብ የወል አድርገን ለውጡ አሸንፎ እንዲወጣ ያስቻሉ ንድፎች የተቀመሩበት ቅጽ ነው።
የመደመር ትውልድ የተሰኘው ሦስተኛው ቅጽ ከፍ እያለ መጥቶ የመደመር ሐሳብ የትውልድ ሐሳብ እንዲሆን፣ ለኢትዮጵያዊ ትውልድ የምንመኘውን እና ለኢትዮጵያ ይበጃል ያልነው ሐሳብ የተመላከተበት ነው። ቅጽ ሦስት የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የሚባለውን ያለፉት 100 ዓመታት ታሪክ በአምስት ምድብ በመክፈል የበየነ መሆኑን እና ለዚህም የተጠኑ ባሕርያት መኖራቸውን ያነሳል። በዚህም መሠረት የመጀመሪያው ትውልድ ወግ አጥባቂ፣ ሁለተኛው ትውልድ ህልመኛ፣ ሦስተኛው ትውልድ ውል አልባ፣ አራተኛው ትውልድ ባይተዋር፣ አምስተኛው እና አሁን ያለው ትውልድ ደግሞ የመደመር ትውልድ ተብለው ተበይነዋል። ትውልዱ በመደመር እሳቤ እንዴት እንደሚታነጽ በቅጽ ሦስት ተቀምጧል። በተጨማሪም ስለ ጥበብ፣ ውበት፣ ‘ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ’፣ ተፈጥሮን በመገንዘብ ተስማምቶ ስለመኖር በዚሁ ቅጽ ተብራርቷል። ብዙ ጊዜ መንግሥታት ያልደፈሩትና የመደመር ትውልድ ደፍሮ ካነሳቸው ሐሳቦች አንዱ የመካከለኛው ምሥራቅ እና ቀይ ባሕር ጉዳይ ነው። የቀይ ባሕር ጉዳይ ሰሞኑን የተነሳ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። በአጠቃላይ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከትውልዱ ምን ይጠበቃል?፣ ምን የቤት ሥራ አለበት?፣ ምን ቢከውን ነው የበለጸገች፣ የተሻለች ፣ የላቀች ኢትዮጵያን መፍጠር የሚችለው የሚለውን ሐሳብ የመደመር ትውልድ በዝርዝር ዳስሷል።
አሁን የተሰናዳው አራተኛው ቅጽ የመደመር መንግሥት ይባላል። በዘመናዊት ኢትዮጵያ ያሉ መንግሥታት የመንግሥታቸውን ቅርጽ፣ የመንግሥታቸውን እሳቤ፣ የመንግሥታቸውን አደራረግ በዚህ መንገድ ሠንደው አስቀምጠው አያውቁም። የመደመር መንግሥት አቀራረብ እና ዝግጅት በኢትዮጵያ ታይቶ አያውቅም። በአፍሪካ ደረጃም በእንደዚህ ዓይነት መልክ መንግሥታቸው ያለው እሳቤ፣ ያተገባበር ስልቱን፣ የሚከወንበትን መንገድ፣ ሊያሳካ የሚያስበውን ግብና ውጤት በዝርዝር ያስቀመጠ እና ለሕዝቡም የገለጸ መንግሥት የለም። ይህ በራሱ ፈር ቀዳጅ ያደርገዋል። የመደመር መንግሥት ዋና ሐሳቡ በጽንስ (በንድፍ) ያየነውን መደመር፣ በፍልስፍና ያየነውን መደመር፣ ታሪኩንና ጉዞውን ያየነውን መደመር፣ ትውልድን እንዴት እንደሚሠራ ያየነውን መደመር ተቋማዊ ቅርጽ እንዲይዝ ያደርገዋል። መንግሥታዊ ቅርጽ እንዲይዝ የሚያደርገው ይህ ሠነድ ነው፤ ሐሳቡ ከግል፣ ከቡድን ወጥቶ እንደ መንግሥት እሳቤው እንዴት እንደሚተገበር በዝርዝር ያስቀምጣል። አንደኛ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚታየው ከዓለም ጋር የት ተላለፍን? እኛ እና የተቀረው ዓለም የተላለፍነው የት ነው? ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ ስብራቶቻችን የት ጀመሩ? በሚል እኛን ከዓለም የለዩንን ነገሮች በዝርዝር ያነሳል። ኋላ ለመቅረታችን ምክንያት የሆኑ ፈተናዎች፣ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? የሚሉትን በዝርዝር ያትታል። በተጨማሪም በእኛ እና በዓለም መካከል የተፈጠረውን ክፍተት እንዴት ልናጠብበው እንችላለን? ምን ዓይነት መደመራዊ አካሄዶች ብንከተል ሊጠብብ እንደሚችል ይተነትናል። ታሪኩን ካነሳ እና ክፍተቱን ከለየ በኋላ አይተውም፤ መጥበብ የሚችሉበትን መንገዶችም ያመላክታል። ያን ለማድረግ ከተለመደው የመቅዳት አካሄድ ተላቅቀን መደመራዊ ፈጠራ፣ መደመራዊ ፍጥነት እና መደመራዊ የዝላይ መንገዶችን መከተል አለብን። ካልፈጠርን፣ ካልፈጠንን፣ በአንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ ካልዘለልን በስተቀር ያንን ክፍተት ለማጥበብ እንቸገራለን ብሎ በዝርዝር ያትታል። ሐሳቡን ሲዘረዝር ከቀደሙ መንግሥታት ኃልዮቶች ጋር ራሱን ያወዳድራል። ለምሳሌ ገበያ መር ባልንበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ያወዳድራል። ወይም የዕዝ ኢኮኖሚ ባልንባቸው ወቅቶች የነበረውን አሠራርና አደራረግ ያወዳድራል። ልማታዊ መንግሥት ያልንባቸውን ጊዜያትም እንዲሁ። እነዚህን ኃልዮቶች በማንሳት በንጽጽር ያነሳል። በሁለተኛነት መደመርን ፍልስፍናው አድርጎ የሚመራ መንግሥት ምን ዓይነት ባሕርያት እንዳሉት በዝርዝር ያስቀምጣል። ስለሚከተለው ስትራቴጂ እንዲሁ በዝርዝር ያትታል። ስለሚያስመዘግበው ውጤት፣ ስለሚኖረው ግንኙነት፣ የዘመነ ገጠር፣ የተሳለጠ ከተማ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ያነሳል። ለስኬታችን ወሳኝ ጉዳዮችንም በሦስተኛነት ያነሳል። የፖለቲካ ስክነት ለኢኮኖሚ ስምረት የሉትን ጭምር። በሌላ በኩል ዕቅዶች እንዳይሳኩ የሚያደርጉ ተግዳሮቶችንም (ችግሮችን) ያነሳል። ድልብ ሐብቶችን እየመነዘርን የምንጠቀምበትን ሁኔታና የመፍትሔ ሐሳቦችን ያመላክታል። የጋራ ትርክት መገንባት፣ ሐሳብ ላይ የሚጫወት የፖለቲካ ምኅዳርን ማስፋት ላይም ያብራራል የሚሉትን እና ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦችንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቃለ ምልልሳቸው ወቅት አንስተዋል።
አቶ አሚ ሙሄ አሊ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በዛሬው እለትም ከቀድሞው የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የስራ ርክክብ አድርገዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአዲሱ ተሿሚ መልካም የስራና የስኬት ጊዜን ይመኛል።
መልካም የስራ ዘመን!
መልካም የስራ ዘመን!
መልካም የስራ ዘመን!
መልካም የስራ ዘመን!
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የ90 ቀን ተግባራቶች በጠቅላላ አመራሩ ተገመገመ
በግምገማው አጠቃላይ የ90 ቀን ዕቅድ የሆኑትን ተግባራት ከስራ ዕድል ፈጠራ፣ ከሌማት ትሩፋት፣ ከኑሮ ውድነት ማረጋጋት፣ የፀጥታ ተግባራት፣ ከአገልግሎት አሰጣጥና የውስጠ ፓርቲ ተግባራት እየተከናወኑ የሚገኙ የ90 ቀን ዕቅድ የተግባራት አፈፃፀም ቀርቦ ዉይይት በማድረግ የ90 ቀን ተግባራት በተሻለ ውጤታማነትና በስኬት እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለባቸው የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ አሳስበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 13 ቀን 2017
የ90 ቀን ተግባራቶች
የ90 ቀን ተግባራቶች
የ90 ቀን ተግባራቶች
የ90 ቀን ተግባራቶች
አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
በዛሬው እለትም ከቀድሞው የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከወ/ሮ ኒእመተላህ ከበደ የስራ ርክክብ አድርገዋል።
መልካም የስራ ዘመን!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
አዲስ አበባን የብልፅግና በር!
ባለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ በየደረጃው ባሉ አመራሮች ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቋል::
በአዲስ አበባ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር እንደ ሀገር ከነበርንበት የቁልቁለት ጉዞ ለማንሰራራት፣ ባለፉት ሰባት አመታት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ስኬቶችን አልቆ ለማስቀጠል ፣ ጉለቶችንም በማረም ለታለመለት ሁለንተናዊ ስኬት ለመድረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለሶስት ቀናት ሲያካሄዱት የነበረውን ውይይት በተሻለ ተነሳሽነት ለላቀ ውጤት ለመትጋት ተግባቦት ላይ በመድረስ አጠናቅቋል።
ሀገራዊ ለውጡ እውን ሲሆን ከተማችን እንዲሁም ሀገራችን የነበሩበት ነባራዊ ሁኔታ ፣ የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን በመሻገር ታሪካዊ ስብራቶችን ለመጠገን የተወሰዱ እርምጃዎች ፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች እና በፈተናዎች ውስጥ የተመዘገቡ አንፀባራቂ ድሎች በውይይቱ ላይ ተዳስሰዋል።
ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የመንግስትን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ የተያዘው አቅጣጫ ተግባራዊ እየተደረገ በመሆኑ ተነሳሽነትን ከፍ የሚያደርጉ ስኬቶች በየዘርፉ መመዝገባቸውም በውይይቱ ተመላክቷል። ለሶስት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ውይይትም የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት እና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የፓርቲያችንን አሻጋሪ እሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀም እንዲሁም ለማስፈፀም ተግባቦት ተፈጥሯል።
ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕያችን አሳታፊ እና አካታች ነው። አመራሩም ፣ አባላትም ፣ ሁሉም ዜጋ በየተሰማራበት ታሪካዊ ኃላፊነቱን በመወጣት አሻራውን ሲያሳርፍ የሀገራችንን ልዕልና የማረጋገጥ ጉዞአችን ይበልጥ ይፋጠናል። መንግስት በሰላም ስራዎች ላይ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ በመቀጠል ፣ የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ ሲሆን ፣ በየጊዜው የሚደረጉ መሰል ውይይቶች ደግሞ ወቅታዊ ፣ ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ በማስያዝ ጭምር ፣ በፓርቲያችን ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ግልፅነት ፈጥሮ ተልዕኮን በተቀናጀ አግባብ ለመፈፀም የጎላ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ይታመናል::
በየደረጃው ያለው አመራርም በአገልግሎት አሰጣጡ ፣ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እና የልማት አርበኛ በመሆን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ለመትጋት ተነሳሽነት በመፍጠር ለተሻለ ስኬት እንደሚሰሩ አንስተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
የመደመር መንግሥት!!
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቃለመጠይቅ!!
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመደመር ሐሳብ ላይ የጻፉት አራተኛውንና "የመደመር መንግሥት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።
የመደመር መንግሥት!!
የመደመር መንግሥት!!
የመደመር መንግሥት!!
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ታላቁን የጋራ ሀገራዊ ገዢ ትርክት ያጸና!!
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሀገራችን ኢትዮጵያ አልፎ ለመላው የአፍሪካ ህዝብ ኩራት የሆነ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ።
ህዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ልዩነት የተሳተፉበት፣ ታላቁን የጋራ ሀገራዊ ገዢ ትርክት ያጸና!! ለሀገራቸው የብልፅግና ጎዳና እውን መሆን በአንድነት የቆሙበት የነፃነት ተምሳሌት የብሄራዊ አርበኝነት መገለጫ ነው።
የህዳሴ ግድቡ በሀገራችን ውስጥ ያሉ ህዝቦች በሙሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ አሻራቸውን ያኖሩበት በዚህ ዘመን ዳግም አርበኛ መሆናቸውን በተግባር ለመላው አለም ያረጋገጡበትን የልፋታቸው ድምር ውጤት ነው ።
ግድቡ ሲጠናቀቅ በከፍተኛ ደረጃ በሀገራችን እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ሸፍኖ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር የሀይል አቅርቦት በማቅረብ የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት የሚያስችል ሁኔታ ይፈጥራል ።
በህዳሴ ግድብ ያገኘነውን ልምድ ተጠቅመን ሌሎች ሀገራዊ ፍይዳ ያላቸውን ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ነድፎ መስራት ከሁላችንም የሚጠበቅ ነው።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር "ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም!" እሳቤዎች እና አሰራሮች ላይ ሰነድ በማቅረብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
"ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም!"
በሚል መሪ ቃል እሳቤዎች እና አሰራሮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
አቶ ለማ ቱሉ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት ተፈጥሯዊ ሆነ ሰውሰራሽ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ለነዋሪዎች በቂ የሆነ ስልጠናዎችና ግንዛቤዎች በመስጠት የሰለጠነ ማህበረሰብ መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል:: አክለውም ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ አካላት በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ምክንያት የተፈናቀሉ እና በስደት ምክንያት ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ሰብዓዊና በጎ አድራጎት ድጋፎች ለማድረግ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በራስ አቅም 70% ሀብት ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የእሳትና አደጋ መከላከል ስራስኪያጅ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳባ ረጋሳ እንደገለፁት ተፈጥሯዊ ሆነ ሰው ሰራሽ በአደጋ ስጋት እንዳይከሰት ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ በቂ የሆነ ግንዛቤ እና እውቀቱ ለነዋሪው በማስጨበጥ የተረጂነት እና ልመና አስተሳሰብ እና መንፈስ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ለማድረግ ባለ ድርሻ አካላቱ ትኩረት ሰጥቶ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል:: ኃላፊው አክለውም የቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት በሀገራችን እንዲሁም በከተማችን የእሳት አደጋዎች፣ የመሬት መንሸራተት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሌሎችም አደጋዎች አልፎ አልፎ እንደሚከሰቱ ያሳወቁ ሲሆን ለዚህም አደጋዎች ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 07 ቀን 2017
"ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም!"
"ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም!"
"ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም!"
"ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም!"
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ በ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ከ11ዱ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ የሶስተኝነት ደረጃን በማግኘት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ቤተልሔም ትዳሩ ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት መረጃ በ2017ዓ.ም የስራ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የሶስተኝነት ደረጃ በመያዝ የዋንጫ እና ሰርተፍኬት ተሸላሚ እንደሆኑ በመግለጽ ለዚህ ውጤት መመዝገብ ጉልህ ሚና ለነበራቸው የክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ጠቅላላ አመራሮች ፣ የዘርፉ አመራሮች፣የክንፋ አባላት እና ባለድርሻ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ ብለዋል።
እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከ11ዱም ክ/ከተሞች በስራ አፈፃፀም ተመዝኖ 1ኛ ወጣ!!
የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ በዝናው ተሾመ ለኮልፌ ኮሙዩኒኬሽን በላኩት መረጃ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ በዓመቱ መጀመሪያ ተቆጥረው በተሰጡት ዓበይት ተግባራት ስራዎች ተመዝኖ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የአንደኝነት ደረጃ በማግኘት የእውቅና ሰርተፊኬት እና ላፕቶፕ መሸለሙን ገልፀዋል።
ጽ/ቤቱ ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ትልቁን እገዛ ላደረጉ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ፣ በየደረጃው ላሉ አመራሮች ፣ የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች ፣ ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር
የታሏቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማጠቃለያ ምዕራፍን በማስመልከት የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ ።
ኮልፌ ወረዳ 07 ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የታሏቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማጠቃለያ ምዕራፍን አስመልክቶ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች፣ የሀይማኖት ተቋማትና የወረዳው ነዋሪዎች በተገኙበት የእውቅና ፕሮግራም ተካሄዷል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱራሐማን ክብረት በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት
ግድቡ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተሳተፉበት ከአድዋ ድል ጋር የሚመሳሰል ታሪክ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት ከመሆኑም በላይ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናን በመቋቋም የይቻላል መንፈስ ያሰረፅንበት የዚህ ትውልድ አሻራ ነው ብለዋል።
አክለውም የህዳሴ ታሪክ የሰራንበት ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ አሻራ ያኖርንበት በማህበራዊ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ታሪክ የሰራንበት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ነው በማለት መልዕክቶቻቸውን አስተላልፏል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እኛ ኢትዮጵያዊያን ጀምረን የጨረስንበት የአብሮነት፣ አንድነት፣ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነት መንፈስ ያጠናከርንበት የይቻላል መንፈስ ያረጋገጥንበት፣ ከኤሌክትሪክ ማመንጫነት አልፎ የተለያዩ የግብርናና ምርቶች ማምረት የጀመርንበት ሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች መስጠት የተቻለበት ነው ሲሉ ገልጸው
አክለውም ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ የሀገራችንን የሀይል አቅርቦት እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። እንደሀገር ታላቅ ፕሮጀክት ማሳካት እንደተቻለና በቀጠይ መስከረም ላይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑም ገልፀዋል።
የታሏቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
የታሏቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
የታሏቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
የታሏቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
ብልፅግና ፓርቲ በስራ ትጋት እና ፅናት በሁለንተናዊ የለውጥ ጎዳና!!
ብልፅግና ፓርቲ የስራ ትጋትን እና ፅናትን የሚያንፀባርቀው በሀገራዊ ልማት እና ብልፅግና በመገንባት ረገድ ነው። ብልፅግና ፓርቲ አጀንዳው "ልማት እና ብልፅግና" መሆኑን አፅንኦት በማድረግ፣ ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ትውልዶች የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ዘላቂ ስራ እንደሚያስፈልግ ያምናል።
ብልፅግና ፓርቲ በቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ወይም የግል ጥቅም ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብን በመግራት ፣ የሀገርን አንድነት እና የህብረተሰብ ግንኙነትን እንደ መሠረታዊ የለውጥ እሴት ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ ህዝቦች በጋራ ዓላማ ለመስራት ፅናት ለማሳየት የሚያበቁበት መንገዶች ናቸው።
የሀገርን ለውጥ ለማምጣት በመስዋዕትነት እና በቀጣይነት የሚደረግ ጥረት ያስፈልጋል ፤ ይህም በተለይ በአስተዳደራዊ፣ በማህበራዊ፣ እና በልማታዊ ሂደቶች ውስጥ የፅናት እና የጊዜ ቆይታ ያለው አቀራረብ ይጠይቃል። ፓርቲው የሚያተኩረው በስኬታማ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው ፤ በዚህም ተግባራዊ ለውጥ ማሳየት ተችሏል።
ብልፅግና ፓርቲ በስራ ፅናት ከአጭር ጊዜ ውጤቶች ይልቅ ዘላቂ ለውጦችን በማምጣት ረገድ አተኩሮ ይሰራል ። በተለይም፣ በሀገራዊ ሪፎርም እና በልማት ሂደቶች ውስጥ የተከናወኑት ለውጦች ለቀጣዩ የእድገት ጉዞ መሰረት እንደሚሆኑ ያሳየ ነው ። ይህም የስራ ፅናትን እና ትጋትን ያሳያል።
እንኳን ደስ አላቹሁ !
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተግባር አፈፃፀም ተመዝኖ ከኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከሚገኙ ከ11ዱም ወረዳዎች መካከል 3ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
አቶ ሰይድ ሙሰማ የኮልፌ ቀራንዮ የወረዳ 07 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት
ይህንን ውጤት እንዲመጣ ከጎናችን ሆናቹ የላቀ ሚና ለተወጣቹ የወረዳችን አስተባባሪ ኮሚቴ፣ አጠቃላይ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ የሰፖርት ቤተሰብ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም
የማታ ጽዳት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ጽዳትና ውበት ጽ/ቤት በየ ብሎኩ የማታ ሺፍት ጽዳት እየተካሄደ አንደሚገኝ ተገለጸ
በፕሮግራሙ ላይ ወ/ሮ ቆንጂት ካሱ የጽዳትና ውበት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ቶላ አብደታ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ደንብ ኦፊሰሮች፣ ባለሙያዎች፣ የጽዳት ማህበራት እንዲሁም የሰላም ሰራዊቶች በተገኙበትም በየ ብሎኩ የማታ ሺፍት ጽዳት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
ወ/ሮ ቆንጂት ካሱ የወረዳው የጽዳትና ውበት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት አካባቢያችን ውብ፣ ፅዱ፣ ማራኪ እና ለኑሮ ተመራጭ ማድረግ የሁላችንም ሚና የላቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 06 ቀን 2017
የማታ ጽዳት ፕሮግራም
የማታ ጽዳት ፕሮግራም
የማታ ጽዳት ፕሮግራም
የማታ ጽዳት ፕሮግራም
አዲስ አበባ: ውብ፣ ፅዱና ምቹ ከተማ!
ከዘመናት በፊት ተቆርቁራ በእርጅና ምክንያት ጉስቁልና አንቆ ይዞ ስሟንና ታሪኳን የማይመጥን ገፅታ የነበራት አድስ አበባ ዛሬ እውነትም አበባ መስላለች። የአፍሪካ መዲናና የበርካታ ዓለምዓቀፍ ተቋማት መቀመጫ የዲፕሎማት መንሃሪያ የሆነችዋ አድስአበባ ማንነቷን በማይገልጽ የአመኮኖሚ፣ የማህበራዊና ገፅታዊ ስብራት ታክማአንፀባራቂና የአፍሪካ ብልጽግናዊ ተምሳሌት መሆን ችላለች። ትውልድ ሲደመርና በህብር ደምቆ በወል ሲተጋ ዕዳን መሰረዝና ምንዳን ማውረስ ይችላል። ስም ይታደሳል፣ ክብርም ይመለሳል ነውና የመዲናዋ ገፅታና ታሪክ ተቀየረ፡፡ አድሷ አድስአበባ የብዙሃን እናት ነችና ዘመንን በዋጀ ህብራዊ ትጋት በአድስ መልክ ለነገ ትውልድ ምንዳ እና ተምሳሌተ ብልጽግና በመሆን እውነተኛ አበባ ሆናለች። መደመር መርህ ሆኖ በመደመር ትውልድ ተሻጋሪ ህልምና ትጋት አድስ አበባ ከጉስቁልና ወደ ልዕልና ተሻግራለች።
ታሪክ ይታደሳል፣ ታሪክ ይሰራል፤ ለትውልድም ዕዳ ሳይሆን ምንዳ ማትረፍ ይቻላል ነውና ለአድስአበባ ዛሬ ትናንት አይደለም። የመዲናዋ የተጎሳቆለ ገፅታዋ በሰው ተኮር ዕሳቤ ተለውጦ ለነዋሪዎች ምቹ ለከተማዋም ተጨማሪ ድምቀት መሆን የሚያስችል ዕምቅ አቅምን በመግለጥ ተዓምራዊ ለውጥን ማምጣት ተችሏል። የአድስ አበባ የተበከሉ ወንዞቿ ታክመው የመስብ ማዕከል ሆነው ሌላ በረከትን አጎናፅፈዋታል። አድስ አበባ ተደምማ ታስደምማለች፤ የኮሪደር ልማቷ፣ ፓርኮችና መናፈሻ፣ የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ፣ የታሪክ መዘክሯ፣ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችና እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ፍጥነትና ጥራትን የአማከሉ ልማቶቿ አስደማሚ ገፅታን አጎናፅፈዋታል። የመደመር ትውልድ ታሪክን ያከብራል፣ ታሪክን ይሰራል፣ ለትውልድም ምንዳን ያሻግራል ነውና አድስአበባ ከተማ ዘመንን በዋጀ የትውልድ ተሻጋሪ ህልምና የጠራ ትልም ታሪኳ ታድሷል። ነዋሪዎቿ እንባቸው ታብሶ ምቹ የመኖሪያ ከባቢ ተፈጥሮላቸዋል፣ ከጎስቋላና ለኑሮ የማይመች መኖሪያ ከባቢ ተላቀው ንፁህ አየር፣ ፅዱ ቤትና ምቹና ተስማሚ ከባቢ ተፈጥሮላቸዋል። አሁን ከተማችን አድስ አበባ ህፃናት ቦርቀውና ተጫውተው የሚያድጉባት፣ ወጣቶች ተዘናንተውና በስብዕና በልጽገው ነጋቸውን የሚገነቡባት፣ አዛውቶችና እናቶች መርቀውና ተጡረው የሚኮሩባት፣ ነጋዴዎች ሰርተው የሚያተርፉባት የትውልድ ቱርፋት ሆናለች።
የመደመር ትውልድ የትጋት ውጤት የሆነችዋ አድስ አበባ ሀገራዊ ልዕልናን በማላቅ ሁለንተናዊ የማብሰር ማሳያ ነች። ትውልድ ሲደመርና በህብር ደምቆ በወል ሲተጋ ዕዳን መሰረዝና ምንዳን ማውረስ ይችላል። ስም ይታደሳል፣ ክብርም ይመለሳል ነውና ታሪክ ተቀየረ፡፡ አድሷ አድስ አበባ በትናንት ሳትታሰር በዛሬ ትጋት ታድሳና ተገንብታ በድንቅ መሪዎቿ የላቀ ዕሳቤና በልጆቿ የማይዝሉ እጆች ታንፃ ለነገ ምንዳ ሆና ተምሳሌተ ብልጽግና ለመሆን ችላለች። ውቧ አድስአበባ ድህነት የመስበርና ጉስቁልናን የመቀየር የድል አርማ ነች። አድስአበባ ከጉስቁልና ወደ ልዕልና ተሻግራለች። በመደመር ዘመን ተሻጋሪ ዕሳቤ ስሟ ታድሶ ክብሯ የተመለሰው መዲናዋ አድስአበባ የቱሪዝም ማዕከል፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ መነሃሪያና የዲፕሎማት መቀመጫነቷን በማፅናት የሀገራዊ ልዕልና ግንባታ መነሻና የአፍሪካም የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በድንቅ ስራዎች አረጋግጣለች።
ታሪክ ጠብቀው ዘመንን በዋጀ አርበኝነት በላቀ ዕሳቤና በነቃ ትጋት የከተማዋን ስምና ክብር ወደ ሚመጥን ከፍታ እጅን በአፍ በሚያስጭን ፍጥነትና ጥራት አሻግረዋል። አድሷ አድስ አበባ ትናገራለች፦ ታሪክ ተቀየረ እርጅና ተገፈፈ፣ ለትውልድ ኩራትና እራት፣ ድምቀትና ክብር መሆን የምትችል ውብ ከተማ ሆናለች። መደመር እንድህ ነው፦ ያስባል፣ ይፈጽማል ቃልን በተግባር እያፀና ነገን ዛሬ ገንብቶ ለትውልድ ምንዳን ለሀገር ልዕልናን ያጎናፅፋል! በአጠቃላይ አድስ አበባ የትናንት እርጅናን ቀንበር ሰብራ ከጉስቁልና ወደ ልዕልና ተሻግራለች። ለዚህም ነው ማለም፣ ማቀድ፣ አርቆ ማየትና አልቆ መፈጸም የመደመር ትውልድ መገለጫ ነው የምነሰለው። ይህ ትውልድ ታሪክን አድሶ ወርቃማ ታሪክን እየፃፈ ይገኛል። ዘመን ተሻጋሪ ህልምን አንግቦ አቧራን ያራገፈና አሻራን ያሳረፈ ትውልድና ነውና በህብር ደምቆ በወል እየተጋ ሀገራዊ ልዕልና እውን ያደርጋል። በደም የከበረቸዋን ሀገር በላቡ እያፀና በአንፀባራቂ ድሎቹ ሳይዘናጋ በወል እውነት የፀናች ልዕልናዋ የተበሰረ ሀገር ይገነባል።
እንኳን ደስ አላቹሁ !
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተግባር አፈፃፀም ተመዝኖ 95% በማምጣት ከኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከሚገኙ ከ11ዱም ወረዳዎች መካከል 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ እንዲሁም የእውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
አቶ ደገሙ ደንድር የኮልፌ ቀሬንዮ የወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት ይህንን ውጤት እንዲመጣ ከጎናችን ሆናቹ የላቀ ሚና ለተወጣቹ የወረዳችን አስተባባሪ ኮሚቴ፣ አጠቃላይ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ በጎ ማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 06 ቀን 2017
የወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
የወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
የወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
የወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ታላቋን ኢትዮጵያ እውን እያደረገ ያለ ፓርቲ ፡- ብልጽግና!!
ብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚሸረሽሩ ትርክቶችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራረቡና የሚያስተሳስሩንን እውነታዎች በማጉላት፣ ከትናንት ጠቃሚ ትምህርቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዛሬና ነገ ላይ በማተኮር ወንድማዊና እህታዊ ህብረትን በብሔሮች መካከል ማጠናከርን ይመርጣል።
ብልፅግና ፓርቲ ሃገራዊ አንድነትን መትከል አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት መዘርጋት ትልቅ ራዕይ አንግቦ የተነሳና ራዕዩም እውን እያደረገ የለውጥ ጉዞውን በውጤት እያረጋገጠ የመጣ ፓርቲ ነው።
የለውጡ ትልቁ ግብ ከሆነው አንደኛው የዲሞክራሲ ማበብ ባህሉን በማስፋት ረገድ የማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና ጋ አስፍቶና አልሞ በመስራት ከፓለቲካ እስረኝነት በመውጣት ለሀገር አንድነትና ለሀገር ሁለንተናዊ ለውጥና ብልጽግና ማረጋገጥ ያስችል ዘንድ አስፍቶ በማሰብ እምርታ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል ሁኔታ ለዘመናት እስር ቤት የታሰሩትን መፍታትና የሀገር የለውጡ አካል እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉ፣ በተለያዩ ጊዜያት በሽብርተኝነት ተፈርጅ ወደ ውጪ አገር የወጡና ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው የነበሩ ነፃ በማድረግ ለሀገራቸው ለውጥ በአንድነት ቆመው የለውጡ ተዋናይ እንዲሆኑ እድል የሠጠ ስርዓት ያበጀ ሂደት ፓርቲ ነው።
የዲሞክራሲ ምህዳሩና ባህሉ የበለጠ እንዲያብብና በተግባር እንዲተገበር ሁሉም ኢትዬጵያዊ ዜጋ አንድ ላለችን ሀገር በመምከር የተፎካካሪ የጋራ ምክር ቤት ተቋም መፍጠር በተያዙ እሳቤዎችንና አላማዎች ላይ ግልጽ የሆነ ውይይት ነፃ ሀሳቦችን በማቅረብ ለውጡን ለማበብ ፈርቀደጃ ስራዎች ለመስራተ ተችሏል።
አቃፊነትን በተግባር ያሳየና ከማሳየትም ባለፈ ቀግልጽ በተጨባጭ ሆኖ በመገኘት የሚታይ እምርታዊ ውጤት የተመዘገበበት እሳ ነው። ለዚህም ከአጋርነት በመውጣት ስለ ሀገር ጉዳይ በእኩል በመሳተፍ እኩል ሀሳብ በመስጠት እኩል በመስራት በእኔነት ስሜት በመስራት ለለውጥ ማረጋገጥ ትልቅ ስራ መስራት ተችሏል።
ለዚህም በህብረ ብሄራዊ አንድነት በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መርህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በማሳተፍ ሁሉም ብሄረሰብ ያሳተፈ ሁሉም ዜጋ ባሳተፈ መልኩ ዲሞክራሲን በመትከል ስራዎችን በውጤት በመቀየር ትልቅ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት ተችሏል።
ሌላኛው የፍትህ እና የሚዲያ ተቋማት ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ ገለልተኛና በማድረግ የተቋማቸውን ህልው በማስጠበቅ ህግና ስርዓቱን በሚጠብቅና በሚያከብር መልኩ ተልዕኮዋቸው በነፃት እንዲመሩ የተደረገበት አግባብ በዲሞክራሲ ምህዳሩ ከማስፋት አንፃር ትልቅ እምርታዊ ለውጥ የመጣበት ሂደት እጅግ የሚበረታታ ነው።
ጠንካራ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች ለዉጤታማ የተግባር ምዕራፍ መሠረት ናቸው!
በብልጽግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት የ2017 የአባላት ግምገማ እና የ2018 በጀት አመት የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት በፓርቲ ኮሚቴ ተገምግመዋል።
የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን በተገቢው በማጠናቀቅ የተግባር ምዕራፍ ስራዎችን በውጤት መፈፀም ያስችላል የሚል ሀሳብ በግምገማ መድረኩ የተገለፀ ሲሆን ተግባሩ ከመልሶ ማደራጀት እስከ አባላትና የተቋማት ዕቅድ የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት ተገምግሟል።
በቀጣይ ተግባር ምዕራፍ ላይ ሲገባም የተሻለ ውጤት እንደሚመዘገብም የታመነበት የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራቱ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባትም የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ይሆናል ተብሎም እንደሚጠበቅ ተገልፆል።
ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባትም የመልሶ ማደራጀት ተግባር ወሳኝ በመሆኑ በዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቅ ያለባቸውን ጉዳዮች በማየት እንዲጠናቀቁ ማድረግም ተገቢነት አለው ። የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች የውስጠ ፓርቲ ስራዎችን በተገቢው በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና ስላላቸው መረጃዎችን በተገቢው ማደራጀት ይገባል ብለዋል የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 05 ቀን 2017
የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት
የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት
የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት
የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቡን በማስተባበር በራስ አቅም የጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። የኮሪደር ልማቱ በአሁኑ ሰዓት እግረኛ መንገዶችን፣ ፋውንቴን ግንባታዎችን፣ የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን እና የካፌ ግንባታዎችን በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህ ፕሮጀክት የህንጻዎች ደረጃ ማሻሻያ (standardization)፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች (greenery) ልማት፣ በእግረኛ መንገዶች ላይ የቴራዞ ንጣፍ ዝርጋታ፣ የመናፈሻዎችና የፋውንቴኖች ግንባታ፣ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰትን የሚያቀላጥፉ የትራፊክ መብራቶች ገጠማ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ነው።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የተጣመረ የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም የመብራት፣ የውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን ያጠቃልላል። ከእነዚህ ስራዎች በተጨማሪ ማስታወቂያዎችን ወደ ዲጂታል መቀየርና የመኪና ማቆሚያ (parking) ስፍራዎችን ማዘጋጀትም የኮሪደር ልማቱ አካል ናቸው።
ለህዝብ የገባውን ቃል እውን ማድረግ የቻለ ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ !!
ኢትዮጵያ ከሀገራዊ ምስረታዋ ጀምሮ የመደመር መርህ ያሳየ የሚመስል አብሮ የመኖር ጥብቅ ትስስር ያለው ቢመስልም በወቅቱ ከአራቱም የሀገራችን አቅጣጫዎች ለሚነሱት በቂ ከሀገር የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ባህላዊ ፣ ስነልቦናዊ እኩል እያደገ ያልመጣው የጥያቄዎች ምላሽ በየዘመኑ ለገጠመኑን ብዙ ውስብስብ ውስጣዊ ችግሮች ተጋላጭ አድርጎናል ። ይህንን ስብራት ጠንቅቆ በመረዳት በቂ የትርክት ግንባታ ዝግጅት ያደረገው ፓርቲያችን ብልፅግና በእያንዳንዱ ዘርፍ የገጠመንን ችግር በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው መሰረቱ ሀገራዊ መግባባት ላይ ያደረገ የሁሉም ከሁሉም ለሁሉም የሆነች ሀገርን በማፅናት መሆኑን በተግባር በማረጋገጥ ነው ።
ከሀገራዊ ውክልና ጀምሮ ህብረብሄራዊነትን መነሻ ባደረገ መልኩ በመስራት ፣ ነፃ ጠንካራ እና ገለልተኛ ተቋማትንም በማበራከት ፣ ፕሮጀክቶችን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነትን ጨምሮ በማጠናቀቅ ፣ የትምህርት ስርዓታችንን ለትውልድ መሰረት አድርጎ በማዋቀር ፣ ገዥ ትርክት የሁሉም ተግባር መሰረቱ በማድረግ ፣ የሀገርን ህልውና በማስቀጠል በበቂ ምክንያት ላይ መሰረት ያደረገ የሚዲያ ነፃነትን ማረጋገጥ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን በመከተል የህዝብን ቅቡልነት ያገኘው ለሁለንተናዊነት የሚሰራው ፓርቲያችን ብልፅግና አሁንም ለተጨማሪ ድልና ስኬት በመደመር መንገዱ ላይ ይገኛል ።
የአብሮነታችን ክታብ ፣ የከፍታችን ፍኖት : ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ !
ከአስሩ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ከ80 በመቶ በላይ የውሃ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ ምንም የውሃ ድርሻ እንዳይኖራት የተለያዩ ሴራዎች ሲጠነሰሱ ኖረዋል።
ለዓባይ ወንዝ ህልውና ምንም አስተዋፅዖ የሌላቸው ሁለቱ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ደግሞ ብቻቸውን መጠቀም እንዲችሉ በግልፅም በስውርም ጥረቶች ተደረገዋል ፤ ይህ ፍርደ ገምድልነት የነበረው ኢፍትሀዊ የዓለም ስርዓት ነፀብራቅ ነው። ነፃነት ፣ እኩልነት ፣ ፍትሀዊነት የሚባሉ የዴሞክራሲ እሴቶች ከፍ ብለው በሚሰሙበት በዚህ ወቅት ጭምር ኢትዮጵያን ባይተዋር አድርጓት የቆየው አግላይ የቅኝ ግዛት ዘመን ውል ተፈፃሚ እንዲሆን የሚጥሩ መኖራቸው ደግሞ ግርምትን ያጭራል። ከውስጥ ችግሮች እና ስር የሰደደ ድህነት ጋር ሆኖ ለሀገራችን ተጨማሪ ዕዳ ሆኖ የቆየው የቅኝ ግዛት ውል ህጋዊ መሰረት እና አሳሪነት የለውም። የተፈጥሮ ሀብታችንን በብቸኝነት ሲጠቀሙ የነበሩ ሀገራት ላለፈው ካሳ መክፈል ሲገባቸው ዛሬም እንደ መከራከሪያ በማቅረብ በሀሳብ ትናንት ላይ ተቸክለዋል።
በተፈጥሮ ሀብታችን የበይ ተመልካች እንድንሆን ኢትዮጵያ በሌለችበት የተፈረመው አግላይ ውል እንኳንስ በአባት እናቶቻችን ክቡር መስዋዕትነት ቅኝ ባልተገዛችው ሀገራችን ፣ በቅኝ ግዛት ስር በነበሩ ሀገሮችም ጭምር ተግባራዊ መደረግ የማይችል መሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው። ከዚህ እውነታ በመቃረን ዛሬም ትናንት ላይ ቆመው የቅኝ ግዛት እሳቤን የሚቃዡ አሉ። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በፍትሀዊነት አልምታ ለመጠቀም የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደ ስጋት የሚቆጥሩ እና የሚያጣጥሉ አካላት የኢትዮጵያን ፈጣን ዕድገት ለመግታት በስውርም በግልፅም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቀጥሏል። ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ እያደገ በሚገኘው ፈተናን ወደ ድል የመቀየር ባህላችን የታሪካዊ ጠላቶቻችን ሴራ የኢትዮጵያውያንን ቁጭት የተሞላበት የልማት ጉዞ ወደ ፊት ያስፈነጥረዋል እንጅ ወደ ኋላ የመመለስ አቅም የለውም።
ኢትዮጵያን ለማሻገር ቆርጦ የተነሳው የመደመር ትውልድ ለፈተናዎች አይበገርም። መዳረሻው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ በመሆኑ በተገኙ ውጤቶችም ረክቶ አይቀመጥም ፤ አዳዲስ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ይበልጥ ይተጋል። በታላቁ ወንዛችን ላይ እየተገነባ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን በተባበረ ክንዳችን የማያልፉ የሚመስሉ ውስብስብ ችግሮችን ተሻግሮ ለፍሬ በቅቷል። የኤሌክትሪክ ብርሃን ማመንጨት ከጀመረ የሰነባበተው ታላቁ ግድባችን የአሳ ጎተራ መሆንም ችሏል። ለአካባቢው ስነ ምህዳር መጠበቅ ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ ተሞክሮ የሚቀሰምበት ፣ ለመዝናኛም ተመራጭ የቱሪስት መስህብ መሆኑም ከቱሩፋቶቹ መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
ኢትዮጵያዊያን በገንዘብ ፣ በእውቀት፣ በጉልበት እና በመሳሰሉት ደማቅ አሻራቸውን በማሳረፍ በራስ አቅም የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብዝሀ አብሮነታችን የሚጠብቅበት አስተሳሳሪ ትርክታችን በመሆኑ በዛሬው ብቻም ሳይሆን በመጪው ትውልድ ጭምር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ማርሽ ቀያሪ ፕሮጀክት ነው፡፡ ከበርካታ አስርት ዓመታት በፊት ተወጥኖ ፣ በሚሊኒየሙ ማግስት የተበሰረው ፤ ለመቆም ከተቃረበበት አስቸጋሪ ሁኔታ ወጥቶ በሀገራዊ ለውጡ ለፍፃሜ የበቃው እና ምርቃቱ በቅርቡ የሚበሰረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች አሉት የምንለውም የብሔራዊ ጥቅም እና የብሔራዊ ክብር ጉዳይ በመሆኑ ነው።
ከነበሩበት ውስብስብ ማነቆዎች ተላቅቆ ፣ እንደ ወርቅ ነጥሮ ከጉባ ሰማይ ስር የፈነጠቀው ብርሃን በጨለማ ተውጠው ከኤሌክትሪክ መብራት ጋር ሳይተዋወቁ የቆዩ አካባቢዎችን ተቋዳሽ ያደረገ ፣ የሁሉንም ተስፋ ያለመለመ ነው። በተፈጥሮ ሀብታችን ባይተዋር ሆነን የቆየንበት ዘመን ማብቂያ ብስራት ፤ በራስ አቅም የመለወጥ ፣ የማደግ እና የመበልፀግ የአይበገሬነት አብነት ነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ። አባት እናቶቻችን ወራሪ ሀይሎችን በተባበረ ክንዳቸው ድል አድርገው ፣ ሉዓላዊነትን አስጠብቀው ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ ማድረግ እንዳስቻሉን ፣ የድህነትን አስከፊ እና አሳፋሪ ገፅታ ድል አድርገን የተሟላ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደምንችል ያሳየንበት የላብአችን ጠብታ ውጤት ነው ግድባችንን።
ብንጀምረውም ማጠናቀቅ እንደማንችል ተስፋ አድርገው የነበሩ እኩይ ሀይሎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአቅም ማጣት እንዲሁም በትብብር ጉድለት ምክንያት ለፍፃሜ አይበቃም የሚል ምኞት እንደነበራቸውም አይዘነጋም። በተለይም ሀገራዊ ለውጡ ሊመጣ አካባቢ በተለያዩ ብልሹ አሰራሮች ምክንያት ግድቡ ገብቶበት የነበረው ውስብስብ ችግር እና የመቆም አዝማሚያ ኢትዮጵያ ከድህነት ቀምበር እንዳትወጣ ለሚሹ አካላት ሰርግና ምላሽ ነበር። የአሰራር ማስተካከያ ተደርጎ ፣ ግድቡ የነበረበት ውስብስብ ችግር ተወግዶ እንደ አዲስ ወደ ተሟላ የስራ እንቅስቃሴ የተገባበት ወቅት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን መርዶ ፣ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ብስራት ሆኗል።
የህዝባችን የዘመናት ቁጭት ፍሬ አፍርቶ በተለይም ግድባችን ሀይል ማመንጨት ሲጀምር ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ጉዞ ወደ ፊት ሲንደረደር ፣ ኢትዮጵያውያን በተስፋ ብርሃን ሲሞሉ ፣ የእኩይ ሀይሎች እኩይ ዓላማ ጨልሟል። የዓለም አቀፉን የዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት ፖሊሲ አቅጣጫ የተከተለ ታዳሽ ሀይል መሆኑ እየታወቀ ፤ ከጉባ ሰማይ ስር የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ግድባችን ሀገር አውዳሚ የኒውክለር መሳሪያ ይመስል የዓለም አቀፍ ፖለቲካ የስዕበት ማዕከል እስከመሆን መድረሱ ብርቱ ትግል የጠየቀ ለመጪውም ትውልድ ጭምር ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው፤ በታሪክነቱም ሲወሳ ይኖራል። ታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ ሌሎችም ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲስተጓጎሉ መንግስት ከዛም ከዛም በሚፈጠሩ ግጭቶች እንዲጠመድ የውስጥ ባንዳዎችን እና ተላላኪዎቻቸውን በመጠቀም ታሪካዊ ጠላቶቻችን ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም፤ እንደ ትናንቱ ሁሉ እንደማይሳካላቸው ቢታወቅም ዛሬም መፍጨርጨራቸውን አላቆሙም።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፈተናዎችን ወደ ድል ከቀየርንባቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንጅ ብቸኛው ባይሆንም የሀገርን ሉዓላዊነት የሚፈታተኑ ጫናዎችን አስተናግዶ እንደነበር አሌ የማይባል ሀቅ ነው። ፈተናዎች ይበልጥ እያበረቱን ፣ ተግዳሮቶች ሳይበግሩን አቅሞቻችንን አስተባብረን በመነሳታችን አባት እናቶቻችን በዓባይ ወንዝ ላይ የነበራቸው የዘመናት ቁጭት ወደ ፍሬ እንዲቀየር ማድረግ የተቻለበት የታሪክ እጥፋት ሆኖም ተመዝግቧል። በራሳችን አቅም መበልፀግ እንደምንችል ያመላከተ ፣ ተግዳሮቶች እንደማያስቆሙን ያረጋገጠ ፣ እንደ መጀመርያው የአርበኝነት ምዕራፍ ሁለተኛው የአርበኝነት ምዕራፍም በድል እንደሚጠናቀቅ የጠቆመ የኢትዮጵያ ከፍታ ማስፈንጠሪያ ጭምር ነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ።
የሀገርን ሉዓላዊነት ለመዳፈር የመጣውን የጠላት ሀይል በአብሮነታችን በመቆም በተደጋጋሚ አሳፍረን እንደመለስን ፤ አንገታችንን ያስደፋንን ፣ የሀገራችን መገለጫ እስከ መሆን የደረሰውን ጥልቅ ጉስቁልና እና ድህነትንም በማስወገድ ሁለንተናዊ ብልፅግናችን ለማብሰር ቃላችንን የምንጠብቅበት የአይበገሬነታችን ማፅኛ ፣ የአብሮነታችን ማስተሳሰሪያ ነው፡፡ቀጣይነት ያለው ልማታችን ፍኖት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዘላቂ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራችንም ማህተም ነው። የዚህ ትውልድ አኩሪ ድል ፣ የመጪው ትውልድ ታሪክ የሆነው ይህ ሀገራዊ ፕሮጀክት የተደመረ አቅም ሀገርንም ህዝብንም ከማንኛውም ተግዳሮት ከፍ አድርጎ ማሻገር እንደሚችል አሳይቷል። በሀገራዊ ልማት ሁሉም ዜጋ አሻራውን ማሳረፍ ከቻለ አይቻልም የተባለው ተችሎ ላቅ ያለ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገብ እንዲሁም የኢትዮጵያን ልዕልና ማብሰር እንደሚቻልም አንዱ ማሳያ ነው በቅርቡ የሚሞሸረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ።
አዲስ አበባ በነዋሪዎቿና በመሪዎቿ ትጋት እንደ ስሟ አበባ እየሆነች ያለች ከተማ !!
አዲስ አበባ ቤታችን የሚመጥናትም የሚገባትም ብልፅግና በመሆኑ ዕድሜ ያገረጃ ፋቸው ሰፈሮቿ እየታደሱ፣ አዳዲስ ህንፃዎችም በግሉ ዘርፍ እና በመንግስት በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ግልፅ አሰራር ተዘርግቶ እየተሰራ ይገኛል።
በበርካታ ሰፈሮች በቆርቆሮ አጥር ተሸፍኖ የቆየውን ዝገቷን በመሞረድ ፣ ውቢቷንና ምቹዋን አዲስ አበባን ማነፅ ጀምረናል፤ ማራኪ የአይን ማረፊያ ማድረግ ጀምረናል።
ዘመናዊ የመንገድ ግንባታችን ነገንም ታሳቢ በማድረግ እየተከናወነ ሲሆን አደባባዮቿም የትራፊክ ፍስሰቱን ከማሳለጥ በተጨማሪ ውበትን እንዲጎናፀፉ አበረታች ስራዎች እዚህም እዚያም ተጀማምረዋል።
አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ህይወት በሚያሻሻል መልኩ ጎስቋላ ሰፈሮቿ እየታደሱ ተወዳዳሪነቷና ተመራጭነቷ በእጅጉ ጨምሯል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገትን ለማሳለጥ በተሰራው ስራ ሶስት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን አሸንፋ ተሸልማለች።
የአድዋ ሙዚዬምን የመሳሰሉ ታላላቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች ከልማት ፋይዳቸው ባሻገር የኢትዮጵያ ታሪክ ለዓለም ከፍ ብሎ እንዲታይ ጉልህ ሚና የተወጡ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ በስም ብቻ ሳይሆን በሚታይ በሚዳሰስ ልማት መፍካት እንደሚገባት በማመን ፓርቲያችን፣ ህዝባችንና መንግስታችን ከተማዋን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ 24 ሰዓት ስራ ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌት ... !!
ከተማችን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም መስኮች ከፍተኛ ለውጥ እያሳየች ሲሆን በተለይም ድሮ የምናውቀው ይጨናነቅ የነበረው የአዲስ አበባ መንገድ ዛሬ ላይ የትራፊክ ፍሰቱን ለመቀነስ የንግድ ስርዓቱን ለማሳለጥ መንገዶች እየተስፋፉና እየዘመኑ ነው።
ሌላኛው የከተማችን ለውጥ አዳዲስና ዘመናዊ ህንጻዎችና የንግድ ቦታዎች በስፋት እየተገነቡ ሲሆን ይህም ለከተማው የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአኗኗር ዘይቤን ለማሻሻል የተሰጠው ትኩረት አዳዲስ መናፈሻዎችና መዝናኛ ቦታዎችን፤ የመኪና ፓርኮችን፣ የባስ ተርሚናሎችን እና መሰል በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን እየተፈጠሩ ሲሆን ይህም ሰዎች በነጻ ጊዜያቸው የሚዝናኑባቸውን ቦታዎች እያሳደገ መጥቷል።
አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ማራኪ የአፍሪካ መዲና የብዙሀን ቱሪስቶች መዳረሻ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የጽዳት ሥራዎችን በማከናወን፣ አረንጓዴና ውብ ለማድረግ ከተማዋን ይበልጥ ለማዘመን ከፍተኛ ስራም እየተሰራ ነው። በአጠቃላይ አዲስ አበባችን እጅግ አስደናቂ ለውጥ እያሳየች ነው፣ ይህም ለነዋሪዎቿ የተሻለ ሕይወት ለመፍጠር ያለመ ነው። እነዚህን ለውጦች በዘላቂነት ለመጠበቅና ያሉትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ደግሞ የሚጠበቅ ይሆናል።
ለረጅም ጊዜ የህብረተሰቡ መልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረው የውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ 95% መጠናቀቁን አስተዳደሩ ገልጿል
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ እንዲሁም የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰሩ ከሚገኙ ሰራዎች መካከል አንዱ የሆነው የውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ ያለበት ደረጃ ጉብኝት አካሄዱ
አቶ ለማ ቱሉ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ በምልከታም ወቅት እንደተናገሩት ነዋሪው ህብረተሰብ በተለያዩ ጊዜያት ከሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ አስተዳደሩ ጊዜ የለኝም መንፈስ በቁርጠኝነት በፍጥነትና በጥራት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙን ገልጸዋል።
አክለውም ይህንን ስራ ስንሰራ የአመራሩ፣ የባለሙያዎች፣ የባለድርሻ አካላትና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ተናግረዋል
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 04 ቀን 2017
የኮብልስቶን ንጣፍ
የኮብልስቶን ንጣፍ
የኮብልስቶን ንጣፍ
የኮብልስቶን ንጣፍ
ብልጽግና ከትናንት የተማረ ነገን ያሣመረ ትርክት ያነገበ ፓርቲ ነው!!
ብልፅግና ብዝኃነታችንን ያከበረ፤ አንድነታችንን ያስተሣሠረ ፓርቲ ነው። ከትናንት የተማረ ነገን ያሣመረ ትርክት ያነገበ ፓርቲ ነው። የጠላትን አፍራሽ ትርክት ለመመከትና የእኛን ትርክት ለማጋባት ዲጂታል ዐርበኝነትን በሚገባን ልክ እንጠቀማለን። ጠላት የሀገርን አንድነት ለማፍረስ እና ብልጽግናዋን ለማደናቀፍ በበቀል ስሜት አፍራሽ ትርክት ሰንቆ ተነሥቷል። እኛ ማንነታችን የተሣሠረበትን እና ርዕያችን የተሰነቀበት ትርክታችንን ለሕዝብ ለማጋባት ዐርበኛ ልንሆን ወስነናል።
የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት
እኛ የምንወደው ሀገር፣ የምንቆምለት ሀገራዊ ዓላማ እና ሕልም አለን!!
የምናገለግለው ሕዝብ አለን። የምንገነባው ሀገር አለን። የሚናስከብረው ብሔራዊ ጥቅም አለን። ጠላት ደግሞ እነዚህን ሁሉ ማጥፋት፣ ለማፍረስና ለማሰናከል ይፈልጋል። ማልማት፣ መገንባት እና ማጽናት፤ ከማጥፋት፣ ከማደናቀፍ፤ ከማሰናከል እና ከማፍረስ በላይ ዐቅምና ትጋት ይጠይቃል።
የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት
ጤናማ፣ በሚገባ የተጠበቁ የወንዝ ዳርቻዎች የከባቢ ሥርዓትን እና የውሃ ጥራትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን የኑሮ ደህንነት የሚያሻሽሉ እና የከተሞችን ለፈተና አለመበገር የሚያጠናክሩ ደማቅ ሕዝባዊ ሥፍራዎችን ይፈጥራሉ።
ዛሬ ከሰዓት ከብልጽግና ምክር ቤት ስብሰባ በኋላ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሥራ ሂደትን በጋራ ተመልክተናል። ይኽ ሥራ አሁን በተያዘው ምዕራፍ በአምስት ክፍለ ከተሞች የሚዘልቅና 21.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው። ፕሮጀክቱ በጥቂቱ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገፍ፣ ሕዝባዊ ፕላዛዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፣ ሱቆች እና አምፊቴአትሮች የተካተቱበትም ነው።
ከዚህ ግዙፍ ሥራ አላማዎች መካከልም የወንዞች ብክለትን ማስወገድ፣ የከተማዋን የጎርፍ ተጋላጭነት መቀነስ፣ ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን ቁጥር መጨመር እና የሥራ እድል መፍጠር ይገኙበታል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አካባቢያችንን ከመጠበቅ ባሻገር ለአዲስ አበባ ደማቅ እና ዘላቂ የወንዝ ዳርቻዎችን በማስገኘት የከተማዋን ኢኮኖሚ እና የኑሮ ደረጃ ከፍ ያደርጋል።
:-ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ
የወንዝ ዳርቻዎች
የወንዝ ዳርቻዎች
የወንዝ ዳርቻዎች
የወንዝ ዳርቻዎች
የብልፅግና አመራር የኢኮኖሚም የግንባርም ዐርበኛ ነው!!
ብልጽግና ብዝኃ ዐርበኝነትን ይጠይቃል። የደም ብቻ ሳይሆን የላብ መሥዋዕትነትን ይጠይቃል። ዐርበኝነት እና ዝግጁነት የሀገርን ታሪክ ይቀይራሉ። እኛ የብልፅግና ምክር ቤት አባላት ራሳችን ተግተን ሕዝብንም ለማትጋት ተነሥተናል። ራሳችን ጠርትን ሕዝቡንም ለማጥራት ወስነናል። እንደ ዐርበኛ አመራር በልካችን ለመታገል ቆርጠናል። የብልፅግና አመራር የኢኮኖሚም የግንባርም ዐርበኛ ነው። ሕዝብን ያስተባብራል። በግንባር ይፋለማል። ደጀኑንም ያጠናክራል። እኛም ይሄንን ከወትሮው በበለጠ ለመፈጸም ቃላችንን በድጋሚ እናድሳለን።
የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት
ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ድል እና ኢትዮጵያ የተሣሠሩ ናቸው!!
ድል እና ኢትዮጵያ የተሣሠሩ ናቸው። ነገር ግን ከድሎች ሁሉ የሚበልጥ ድል አለ፡፡ እሱም ድልን በአነሰ ኪሣራ ማረጋገጥ እና ከዘላቂ ውጤት ጋር ማስተሣሠር ነው። ከድል ሁሉ የሚበልጠው ድል፣ ድልን ብቻ ሳይሆን ስትራቴጂያዊ ግብን ጭምር ማረጋገጥ ነው። ዘላቂ ድል ማለት ውስጣዊ ባንዳዎችን ብቻ ሳይሆን ውጫዊ ጠላቶችን ጭምር ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ መርታት ነው።
የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት
ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
አዲስ አበባ የብልፅግናችን ጉዞ ማሳያ !!
አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌታዊነቷን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን በማከናወን የዜጎችን በተለይም የወጣቱን፣ የሴቶችን፤ የአቅም ደካሞችን፣ ህይወት የቀየሩ በርካታ ተግባራት ተከናውኗል። ፕሮጀክቶቻችን ተስፋ ሴጪ ብቻ ሳይሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ለበርካቶች እፎይታን የሰጡ ገና ተመርቆም የበርካቶችን ህይወት የሚቀይሩ እየተከናወኑም ይገኛሉ።
የኑሮ ውድነትን ሊቀንሱ የሚችሉ የብልፅግና እሳቤዎች ወደ ተግባር ተቀይረው በተጨባጭ የህዝባችንን ጥያቄ እየመለሱ ይገኛሉ ። የገበያ ማዕከላት፣ የእሁድ ገበያ፣ የሌማት ቱሩፋት፣ የከተማ ግብርና ውጤቶች፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ የተማሪዎች ምገባ ፥ የምገባ ማዕከላት በሰፊው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል። እንደ ብልፅግና የተናገርነውን ለሕዝቡ ቃል የገባነውን በተግባር እያረጋገጥን የተሰጠንን የሕዝብ አመኔታ በአግባቡ እየተወጣን እንገኛለን። አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት በማድረግ የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን እናደርጋለን።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኩራት የይቻላል፣ የመተባበርና የአብሮነት ተምሳሌት !
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከዚህ ስኬት ሲደርስ እልፍ አእላፍ ችግሮችንና የሴራ ወጥመዶችን ያሳለፈ ሲሆን ግድቡን ለመገንባት ስናቅድና ስንጀምር ጫጫታና ጫናዉ ቀላል ያልነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያውያን ሕልምና ተስፋ ከጅምሩ እንዲጨናገፍ አንዳንድ ሀገራት በጋራ አድመው አሲረውብናል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድንገለልና እንድንነጠል ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቶብናል። ሁሉን አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁመን ግድቡን ወደ ማገባደጃ ምዕራፍ ስንሸጋገርም ዘመቻውን ዳግም በመክፈትና ኃይል በማስተባበር በርካታ ጫናዎች መደረጋቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ።
ኢትዮጵያውያን በጋራ የጀመርነዉና አስፈላጊዉን መሥዋዕትነት ሁሉ የምንከፍልለት የኩራታችንና አንድነታችን መገለጫ ፕሮጀክት በመሆኑ መላው የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍል ይህንን ሀገራዊ ፕሮጀክት በአንድነት ሰርቷል ፡፡
ግድቡን የምንገድበው ማንንም ለመጉዳት አይደለም፣ መነሻችን ሕዝባችንን ከጨለማ ኑሮ ለማላቀቅ በመሆኑ በራሳችን ወንዝና በራሳችን ሀገር፣ በራሳችን አቅም እንዳንለማ የምናደርገውን ስራ ለማጨናገፍ በርካታ ጥረቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል ።
ኢትዮጵያውያን ግን የተለያዩ መሰናክሎችን በጋራ በመቆም እየበጣጠሱ፣ ተማሪዎች ከዕለት ጉርሳቸዉ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ከደመወዛቸው፣ ነጋዴዎች ከወረታቸው፣ ጡረተኞች ከአነስተኛ አበላቸው፣ የጉልበት ሠራተኞች ከዕለት ጉርሳቸው፣ የፀጥታ ኃይሎችና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከሬሽናቸው፣ በውጭ የሚኖሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከአነስተኛ ገቢያቸዉ፣ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በላባቸው ካፈሩት ፍሬ እየቀነሱ ግድቡን ከማጠቀቂያ የምርቃትና ፍሬው ከሚጨበጡበት ምዕራፍ አድርሰውታል ፡፡
ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ አስተዋጽኦ ያደረጉት ገንዘባቸዉን ብቻ አልነበረም፤ በአጠቃላይ ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን ልክ እንደ ዓድዋ ድል መላዉ ኢትዮጵያውያን የተረባረቡበት የወል ድል ነው፤ በጋራ ጀምረን የማንጨርሰው ጉዳይ እንደሌለ ማሳያም ነው ፡፡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት ፕሮጀክቶችን በራስ ዐቅም ጀምሮ የመጨረስ ዐቅም እንዳለን አሳይተናል፡፡ አጠቃላይ ስራዉ አልቆ የምርቃት ምዕራፍና ውጤቱን መላው ኢትዮጵያዊያን የሚቋደሱበት ቀናት ሩቅ እንደማይሆኑ ይታመናል ።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተሳካዉ በመላዉ ኢትዮጵያውያን የእንችላለን መንፈስና የጋራ ጥረት ነው፡፡ ታላቁ የሕዳሴ ግድባችንም የኢትዮጵያን ሁሉ የጋራ ድልና የይቻላል መንፈስ ተምሳሌት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በኢትዮጵያውያን ኅብረት ግድቡ ተጠናቋል፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናችን እውን ይሆናል!
የ90 ቀናት የተግባር አፈፃፀም፣ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እና የውስጠ ፓርቲ ሥራዎች ያሉበት ደረጃ በአጠቃላይ አመራር የጋራ ተደረገ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር አጠቃላይ አመራር በተገኙበት የ90 ቀናት፣ የመንግሰትና የፓርቲ ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ ስራ አቅጣጫ አስቀምጧል። የስራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የኮሊደር ልማት ስራ፣ ገቢ አሰባሰብ፣ የሰላምና ፀጥታ ስራ፣ የበጎ ፈቃድ ስራ፣ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ አሰባሰብ፣ ትምህርት ለትውልድ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ህዝብ ግንኙነት ስራ፣ ECD እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን አስተሳስሮ በቅንጅት ሰርቶ ውጤት በማምጣት ጥንካሬን በማስቀጠል ክፍተቶች በመሙላት በእቅድ የያዝናቸው ተግባር በትኩረት ልንሰራ ይገባል ሲሉ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ ገልጸዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እንደተናገሩት የሌማት ትሩፋት ተግባር አጠናክሮ በማስቀጠል ነባር ተጠቃሚ በማስቀጠል አዳዲስ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወደ ተግባር በማስገባት ምርት ምርታማነት በመጨመር ከሸማችነት ወደ አምራችነት መሸጋገር ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም የብልጽገና ፓርቲ ስራዎች አጠናክሮ በመስራት ጠንካራ ተቋም መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ነሀሴ 02 ቀን 2017
የ90 ቀናት የተግባር አፈፃፀም
የ90 ቀናት የተግባር አፈፃፀም
የ90 ቀናት የተግባር አፈፃፀም
የ90 ቀናት የተግባር አፈፃፀም
እንኳን ደስ አላችሁ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከኮልፌ ቀራንዮ ከሚገኙ ከ11ዱም ወረዳዎች መካከል በተግባር አፈፃፀም ተመዝኖ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅና ሰርተፊኬት እንዲሁም #የሞተር_ሳይክል ተሸላሚ ሆነናል።
አቶ ቦጃ ከበደ የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት
ጽ/ቤቱ ለዚህ ስኬትና ውጤት እንዲበቃ ትልቁን ድጋፍና እገዛ ላደረጋቹ የወረዳ አስተባበሪዎች፣ በየደረጃው ለምትገኙ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ላቅያለ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 29 ቀን 2017
እንኳን ደስ አላቹሁ !
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከሚገኙ ከ11ዱም ወረዳዎች መካከል በተግባር አፈፃፀም ተመዝኖ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
አቶ ከባዱ ሽታ የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስ የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት
ተቋሙ ለዚህ ስኬትና ውጤት እንዲበቃ ትልቁን ድጋፍና እገዛ ላደረጋቹ የወረዳ አስተባበሪዎች፣ በየደረጃው ለምትገኙ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 29 ቀን 2017
የመደመር ትውልድ!!
የመደመር ትውልድ:- ተረጂነትን የሚፀየፍ ፣ የኢትዮጵያን ሉዔላዊነት እና ክብር የሚያረጋግጥ የሁለተኛው ምዕራፍ አርበኛ ትውልድ ነው!! የመደመር ትውልድ፤ ለመፃይ ኢትዮጵያ ዜጋ ውዝፍ እዳን ወደ ምንዳ እየቀየረ ነው። የህዝቦች መከባበር፣ በአንድነትና በአብሮነት ተቻችሎ በመኖር ሀገርን ያፀናል፣ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞም ፅኑ መሰረት ላይ ያኖራል!
የመደመር ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከምግብ እጥረት ወጥተው ለምግብ ጥራት የሚሠራ፤ ጎተራው ሞልቶ የተትረፈረፈ አምራችና ሰጪ ትውልድ፤ መጪዋን ኢትዮጵያ ሊረከብ ይገባል ብሎ ያምናል።
የመደመር ትውልድ የረሃብ ታሪካችንን ለሌሎች በሚደርስ መትረፍረፍ ገልብጦ፤ ኢትዮጵያን የጥጋብና የመትረፍ ምሳሌ የሚያደርግ ትውልድ ነው።
አዲስ አበባ በብልፅግና ጎዳና!
አዲስ አበባ ለእንግዶቿ አይደለም ለነዋሪዎቿ አስደማሚ መሆኗ እንደቀጠለ ነው።ትናንት በእርጅና በኋላቀርነት እና ከደረጃ በታች በሆነው ገፅታቸው የሚታወቁ ሰፈሮቿ በማይታመን የጊዜ ርዝማኔ ፍፁም ዘመናዊነትን ተላብሰው መመልከት የሁልግዜ ተግባር እየሆነ መጥቷል።
ብልፅግና መገለጫው የሆነው ሰው ተኮር እንቅስቃሴም በሚያስገርም አኳኋን በርካቶችን እያሳተፈ እና ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ እያደረገ ቀጥሏል።ተግባሩን ከከተማዋ ነዋሪ ጋር የሚዛመድ ከሁሉም እምነት እና ባህል ጋር የማይጋጭ በመሆኑ ጉዳዩ ከተራ የተግባር አፈፃፀምነት ይልቅ ባህል መሆን እያደገ የመጣበትን አዝማሚያ እየተስተዋለ ነው።
አዲስ አበባ በብልፅግና ጎዳና ላይ እየተራመደች እንደሆነች በበርካታ መገለጫዎች ማቅረብ ይቻላል።በአዲስ አበባ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከተማዋን የብልፅግና ተምሳሌት ከማድረግ አንፃር ታይቶ ስለሚከናወን በየግዜው አዳዲስ የሆኑ ለውጦች እየተመዘገቡ በርካታ ተግባራት የህዝብን ጥቅም በሚያረጋግጥ አግባብ ተፈፅሟል።
የፓርቲያችንን እሳቤዎች በተጨባጭ ወደ መሬት በማውረድ በከተማው ስር የሰደደ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ችግሮችን ከስር መሰረቱ ለመፍታት የሚያስችል ቁመና በመያዝ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ መገንባት ተችሎአል።
የነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህጻናት ምቹ የመጫወቻ ቦታ ማዘጋጀት እጅግ አስፈላጊና ልጆች በአካላዊ እና በአእምሮአዊ የዳበሩ ያደርጋል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደርም ለነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህፃናት ትኩረት በማድረግ ቀዳማይ ልጅነት የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን በመገንባት ህፃናት በአእምሮና በአካል የዳበሩ እንዲሆኑ ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በእነዚህ የመጫወቻ ቦታዎች ህፃናት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ አካላቸውን ያዳብራሉ፣ ይህ ለጤናማ የሰውነት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
የልጆችን የማህበራዊ ግንኙነት ችሎታ ያጎለብታል።
በተጨማሪም አብረው ሲጫወቱ አዳዲስ ነገሮችን ይማራሉ፣ ችግር የመፍታትና ፈጠራ የማመንጨት ብቃታቸውም ይጨምራል።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ኩራት!
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያዊያን የተባባረ ክንድ ተገንብቶ ብርሃን ሊሰጥ አባይ ወደ ብርሃንነት እንዲቀየር ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ፍላጎት የመሰረተ ድንጋዩ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ በመደገፍ አሳይተዋል።
ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከደሃ እስከ ሃብታም፣ ከምሁሩ እስከ አልተማረው እንዲሁም በውጪ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከእለት ጉርሳቸው ቀንሰው በመዋጣት እንደ ዓይን ብሌን የሚጠበቅ አሻራ ነዉ።
ለግድቡ እዚህ ደረጃ መድረስ ኢትዮጵያዊያን በአንድ ልብና በተባባረ ክንድ ነዉ። የአባይ ወንዝ ከጉባ ተራሮች ግርጌ ኃይል እንዲያመነጭ በማድረግ ለሀገር ብልፅግና ጉዞን ያፋጠነ ነዉ።
የነበሩ ተግዳሮቶቹን በድል ተሻግሮ ለኢትዮጵያ የብርሃን ተስፋ የፈነጠቀው ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያዊያ እውነተኛ ኩራት በመሆን በብልፅግና ፓርቲ የተሰሩት የልማት ስራዎች ማሳያ ነው፡፡
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት...!!
ከሁሉ በላይ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!
ዛሬ የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡
ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል ከመቼውም ጊዜ በላይ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ዛሬ የምናስመርቃቸው 4 ኪሎ እስክ እንጦጦ ኮሪደር እውነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡
በአገራችን ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት መገኛ ፣ የህዝብ እንደራሴዎች መቀመጫ ፣ የምሁራን አምባ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መገኛ ፣ በአገሪቱ የመጀመሪያው የህክምና ተቋም የካቲት 12 ዘመናዊ ሆስፒታል መገኛ ፣ የመጀመሪያው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሙዚየሞችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና እንዲሁም የከተማችን የእደ ጥበብ ውጤቶች ልህቀት ማዕከል የሆነው ሽሮሜዳ መገኛ ፤ በአጠቃላይ በርካታ ግዙፍ መንግስታዊና ታሪካዊ ተቋማት የሚገኙበት መስመር የሚሸፍነው እና 314 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት የለማ ሲሆን ::
ይህ ኮሪደር ልማት በፊት ከነበረው 32 ሚትር ስፍት ወደ 42 ሜትር የመንገድ የስፋው ፤ 3 ሜትር የብስከሌት መንገድ እንዲሁም 11 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጨምሮ 11 የታክሲ እና የአውቶቡስ መጫኛና ማውረጃዎች ተሰርተውለታል።
ከዚህ በተጨማሪ 20 አረንጓዴ ቦታዎችና 2 ፕላዛዎች እንዲሁም 10 የህጻናት የመጫዎቻ እና 7 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ጨምሮ 9 መጸዳጃ ቤቶች ፣ ከ5 – 13 ሜትር ስፋት ያለው 11.4 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣ 2 (1 ዘመናዊ ሞልን ያካተተ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተገነባ ያለ ተርሚናሎች እና 11 የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች ያሉት እንዲሁም 7 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና 417 ስማርት ፖሎች አካቷል።
ይህንን መስመር መልሶ ማልማት፤ማደሰና ማስዋብ ለአገራችንና ለህዝባችን ታሪክ ያለንን ክብር የሚገልፅ ከመሆኑም በተጨማሪ ከ15 ሺ ለሚበልጡ ዜጎች ጊዚያዊ እና ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር ችለናል፡፡
በፊት የነበረው 751 ሱቆች ሲሆኑ በአዲስ የተሰሩ 770 ሱቆች በመጨመር 1521 ሱቆች በዚህ ኮሪደር የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ልውውጥ እንዲያድግ አድርጓል።
በመጨረሻም ለፕሮጅክቶች ስኬትና በዚህ ደረጃ ዕውን መሆን ቀን ከሌሊት የደከማችሁ ብሎም በተለያየ መንገድ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
• ኮሪደሩ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት 314 ሄክታር፣
• የመንገዱ እርዝመት እስከ ቁስቋም 5.2 ኪ.ሜ የመንገድ መሰረተ ልማት፣
• ከአራት ኪሎ ሽሮ ሜዳ (3.17 ኪሎ ሜትር) በሁለቱም በኩል
ተጨማሪ አንድ ሌን እንዲኖረው ተደርጓል፣
• የመንገዱ ስፋት ከነበረበት በአማካይ 32 ሜትር ስፋት ወጥ ሆኖ 42 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጓል፤
• 3 ሜትር ስፋት ያለው የብስከሌት መንገድ (10.4 ኪሜ) ተሰርቶለታል፤
• ከ5 – 13 ሜትር ስፋት ያለው 11.4 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ (ስታምፕድ ኮንክሪት) ተሰርቷል፣
• 2 (1 ዘመናዊ ሞልን ያካተተ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተገነባ ያለ) ተርሚናሎች እና 11 የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች አሉት፤
• 7 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች አሉት፣
• 417 ስማርት ፖሎች ተተክለዋል።
• የነበረውን የትራፊክ አደጋ ስጋት ከመሰረቱ የሚፈታ ሲሆን በተለይ የታክሲ ተርሚናል እና የአውቶቢስ መስመሮች አመቺ ሁኔታን የፈጠረ እና ለተሳፋሪዎችም ደህንነት ያረጋገጠ ነው ።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያዊያን የአንድነታችን መገለጫ ፣የሁሉንተናዊ ብልጽግና ማሳያ የዛሬ ሳይሆን ለመጭዎቹ ትውልዶችም ለዘመናት የሚዘልቅ የእልውናችን ፕሮጀክታችን ነው።
በህዝባችን የጋራ እርብርብ የተገነባው የህዳሴ ግድብ ባለፉት አስራ አራት ዓመታት መላው የሀገራችን ህዝቦች እንደ አይናቸው ብሌን እየተመለከቱት ያለ ፕሮጀክት ነው ።
ብልጽግና ፓርቲ ፕሮጀክት መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስ መርህ መሆኑን ያሳየበት የአህጉራችን ትልቅ ፕሮጀክት ነው ::
ይህ ፕሮጀክት ዛሬ ላይ አልቆ በመሪዎቻችን ጥበብ ልቆ በውጤት ታጅቧል የጠላቶቻችን ቅስም የሰበርንበት የአብሮነታችን ማሳያ በመሆን በድል ተጠናቋል::
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 07 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከወረዳው የብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር በጋራ በመሆን "በመትከል ማንሰራራት" የ2017/18 ሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እና የጉድጓድ ቁፋሮ መርሀ-ግብር በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ደጋፊ አመራር፣ የወረዳው አመራሮች፣ የህብረት እና ቤተሰብ አመራሮችና አባላት የተገኙ ሲሆን የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የሀገራችንን የአረንጓዴ ሽፋን በማሳደግ ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን አስተላልፏል።
ሐምሌ 21 ቀን 2017
አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገ ተግባር ነው። አሁን ላይ ደግሞ የችግኝ መትከል ባህል ከመንግሥት ቅስቀሳና ከግለሰቦች ጥረት ባለፈ ሀገራዊ ቅርፅ የያዘ ሲሆን ባለፉት ዓመታት እንዲሁም በዘንድሮ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትልቁ ማሳያ ነው።
በዚህም ባለድርሻ አካላት በየፊናቸው ችግኝ ተከላን በማስፋፋት የተፈጥሮ ሚዛንን ለመመለስ እየጎተጎቱ ነው። የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት፣ የምድር መጎሳቆልና የዕጽዋት መመናመን ጉዳይ ያሳሰባቸው ግለሰቦችና ተቋማት በየፊናቸው አመርቂ ተግባራት አከናውነዋል። ኢትዮጵያም በተፈጥሮ ኃብት ጥበቃና ደን ሽፋን በዓለም ላይ ተጠቃሽ ተሞክሮ ሰንቃ ገብታለች።
የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ አብድልባሲጥ ተማም የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ የውስጠ ፓርቲ ሥራዎችን ማጠናከር፣ ሞዴል ተቋማትን መፍጠር፣ እህትማማችነትና ወንድማማችነትን በማጎልበት እንዲሁም ገዥ ትርክትን በማጽናት የተሰሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነትን ለማቅለልና የተሻለ የምርት አቅርቦት እንዲኖር በተተገበሩ ተግባራት፣ የትምህርት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የመሰረተ ልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን ለማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት፣ የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጡ የኢኒሼቲቭ ሥራዎች፣ በተቋማት ቅንጅታዊ ሥራዎች፣ ሕዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በተሰሩ የፀጥታና የሕግ ማስከበር ሥራዎች፣ ውጤታማ እንደነበሩ ተመላክቷል።
የመሰረተ ልማት ስራዎች እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በተለያዩ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ለማኅበረሰቡ ተደራሽ መደረጉ እንደ ጥንካሬ ተነስተዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 18 ቀን 2017
የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞች በሚተከሉበት በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ግንፍሌ ወንዝ አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያውያን በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ባለፉት ስድስት ዓመታት የሰሩትን ታላቅ ገድል በ2017 ዓ.ም ለመድገም ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል እና የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ፅኑ መሰረት በሚሆነው እና የምግብ ሉዓላዊነት ዋስትናን በሚያረጋግጠው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ካለአንዳች ልዩነት እየተሳተፈ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል።
የምንተክለው ለአፈር ጥበቃ ፣ ለስነ ምህዳር ጥበቃ ፣ አካባቢን ከጎርፍ አደጋ ለመታደግ፣ ለጥላ እና ለውበት ብቻ አይደለም ያሉት ክብርት ከንቲባ የምንተክለው ምግባችንንም ጭምር ነው ብለዋል።
ከስድስት ዓመት በፊት የአዲስ አበባ የአረንጓዴ ሽፋን 2 ነጥብ 8 በመቶ እንደነበር ያስታወሱት ክብርት ከንቲባ አሁን ላይ 22 በመቶ አካባቢ መድረሱንና በ2018 ዓ.ም 30 በመቶ በማድረስ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ለማሟላት ብርቱ ጥረት እንደሚደረግ አመላክተዋል።
የከተማችንን ተወዳዳሪነት እና የቱሪስት መስህብነት ለማሳደግ ከሁሉም በላይ ለነዋሪዎች ምቹ ፣አረንጓዴ ፣ ውብ ከተማ ለመገንባት የተሳካ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ከክፍለ ከተማ ካሉ ወረዳዎች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
የወረዳ 07 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰዒድ ሙሰማ ያስተላለፉት መልዕክት ይህ ውጤትና ስኬት እንዲሳካ ከጎናችን የነበራቹ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ባለድረሻ አካለት ላቅ ያለ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 20 ቀን 2017
የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ
አቶ ለማ ቱሉ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደተናገሩት የአባል ምልመላ፣ የቤተሰብ ውይይት እንዲሁም የአባላት ወርሃዊ ክፍያ በመክፈል ፓርቲያችን በሰው ሀይልና በፋይናንስ በማጠናከር ጠንካራ ተቋም መፍጠር ችለናል፣
ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማረጋገጥ ያሉንን ጸጋዎች እና የስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች በመለየት እና በአንድ ማዕከል በመመዝገብ እና አሻራ በማሰጠት የክህሎት ስልጠና በመስጠት መንግስት በሚያወርዳቸው ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ነበር ሲሉ ገልጸው::
የአቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት፣ የቤት ዕድሳት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች ደም ልገሳ፣ ትራፊክ፣ የችግኝ ተከላ እንዲሁም የክረምት ትምህርት ማስተማር ስራዎች የሰራንበት፣ የውስጥ ለውስጥ ኮብል ንጣፍና ጥገና፣ ካልቨርት፣ ዲች በስፋት መሰራት መቻሉ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ለውጥ አምጪ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለአመራሮች እና የሰራተኛው የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ማረጋገጥ መቻሉን ተናግሯል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እንደገለፁት ተግባራቶች በዕቅድ በመመራት፣ በቡድን እና በጋራ አሳትፎ በመስራት፣ ትግል በማድረግ ውጤታማነት ያረጋገጥንበት፣ የአመራርና የአባላት አቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ተግባራቶች በእውቀት በመምራት የአባል ምልመላ፣ የቤተሰብ ውይይት እንዲሁም የአባላት ወርሃዊ መዋጮ በመክፈል ፓርቲያችን በሰው ሀይልና በፋይናንስ በማጠናከር ጠንካራ ተቋም መፍጠር ተችሏል በኪነጥበብና እና በጎዳና የተለያዩ ትርኢት በማዘጋጀት ገዢ ትርክት ለህብረተሰቡ ያሰረጽንበት የወጣቶች እና ሴቶች እንዲሁም የእናት መኖሪያ ክንፍ በማጠናከር ጠንካራ የብልጽግና ተቋም እንዲፈጠር ሰፊ ስራ የተሰራበት ጊዜ ነበር ሲሉ ተናግረዋል
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በከተማ ደረጃ በተካሄደው ዓመታዊ የተግባር አፈጻጸም ምዘና ከ11 ክፍለ ከተሞ መካከል 3ተኛ ደረጃ በመውጣት የመኪና ተሸላሚ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
አስተዳደሩ በበጀትአመቱ ባስመዘገበው ውጤት በዛሬው እለትም ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከክብርት አዳነች አቤቤ እጅ የመኪና ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን ይህ ስኬት የክፍለ ከተማው አመራሮች ፣ ፈጻሚዎች እና ነዋሪዎች የጋራ ጥረት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን።
ይህ ውጤት እንዲመጣ ከጎናችን ለነበራችሁ የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ፣ እንዲሁም ለአመራሮች፣ ለፈጻሚዎችና ለባለድርሻ አካላት ሁሉ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።
‘’ከሁሉ አስቀድሜ ለመላው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ባለሙያዎች ፣ ነዋሪዎች ፣ በጎፍቃደኞች እንኳን ደስ አላችሁ ፤ ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የከተማ አስተዳደሩ ባደረገው የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ምዘና ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች መካከል 3ኛ ደረጃን በመያዝ የመኪና ተሸላሚ ሆኗል፡፡
አስተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት ተቆጥሮ በተሰጠው ተግባራት በከተማ ደረጃ ተመዝኖ 3ተኛ ደረጃ በመውጣቱ የመኪና ተሸላሚ ሆኗል።
ይህ ውጤት እንዲመጣ የበኩላችሁን አስተዋጾ ያደረጋችሁ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የክ/ከተማ እና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ፣ በየደረጃው ያላችሁ ፈፃሚዎች ፣ በጎ ፍቃደኞች ፣ የምክር ቤት አባላትና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከምንም በላይ የኮልፌ ቀራኒዮ እንቁ የሆናችሁ ነዋሪዎቻችን ላደርጋችሁት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
የሁላችሁም ትብብር እና ቁርጠኝነት ባይኖር ኖሮ ይህን ስኬት ማስመዝገብ ባልተቻለም ነበር።
ይህን አስደናቂ ውጤት በማስመዝገብ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የጥረት እና የውጤት ተምሳሌት መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ ስኬት በቀጣይም የተሻሉ ውጤቶችን ለማስመዝገብ የሚያስችል ብርታት እንደሚሆንልን እናምናለን ፣ ወደፊትም ከእናንተ ጋር በመሆን የተሻለች ክፍለ ከተማ ለመገንባት በጋራ እንሰራለን። የ2018በጀት ዓመትን በውጤት እንድናጠናቅቅ ከጎናችን በመሆን ድጋፋችሁ እንዳይለየን በአስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ ::
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፤እንኳን ደስ አለን
ወ/ሮ ኒእመተላህ ከበደ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
አብረን አቀድን ፣ አብረን ሰርተን፣ አብረን ውጤት አምጥተናል !
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት...!!
ባለፉት ቀናት ስናካሂድ የነበረው የከተማችን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አጠናቅቀናል።
በግምገማችንም የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን በማላቅ እና የተለዩ ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተግባብተናል ።
ከተማችን በሁሉም ዘርፍ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሀገራዊና አህጉራዊ ብሎም አለምአ ቀፋዊ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ፤ ስሟና ግብሯ የተናበበ ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንደምንቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የተዋቀረው የምዘና ኮሚቴ በወረዳ 07 በመገኘት በ2017 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ታቅደው የተከናወኑ ግብ ተኮር የተግባራት አፈፃፀም ማጠቃለያ ምዘና ተካሄደ።
አቶ የኔው ሞሴ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት የዛሬው ምዘና ለቀጣይ የተግባር ውጤታማነት ስለሚረዳ ቡድን መሪዎች እንዲሁም ባለሙያዎች እንደ አቅም በመጠቀም የጋራ ውጤት ተግቶ በመስራት ስኬቶችን መጎናጸፍ ይቻላል በማለት ገልጸዋል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ታቅደው የተሰሩ ስራዎች አመራሩ፣ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ እንዲሁም ህብረተሰቡ በቅንጅት በመሰራቱ የተገኙ ውጤቶችና ስኬቶች በማስቀጠል ክፍተቱን መሙላት ያሰፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
3ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት "የከተማ ግብርና ለምግብ ዋስትናና ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ቃል የዘጠና ቀናት መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም አካሄደ።
በመረሃ ግብሩ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቆያ ላሌ እንዲሁም የወረዳ አመራሮችና ነዋሪዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ተካሄደ።
አቶ መቆያ ላሌ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ እንደተናገሩት በእጸዋት እንዲሁም በእንስሳት ዘርፍ ላይ አቀናጅቶ በመስራት ከሸማችነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር ከራስ የምግብ ፍጆታ አልፎ ለገበያ በማቅረብ ለሌሎችም መትረፍ ይቻላል ሲሉ መልዕክታቸው አስተላልፏል።
አቶ ለማ ቱሉ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት በኢኮኖሚ ዕድገቱ የግብርና ዘርፍ ላይ ትልቅ የሚባል አስተዋጽኦ ስለሚያበረክት በእጸዋት እና በእንስሳት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ አስፍቶ በመስራት ለሌሎች ተሞክሮና አርኣያ በመሆን ምርት ምርታማነት በማሳደግ የኑሮ ውድነት መከላከልና የገበያ ማረጋጋት እንደሚቻል ገልጸዋል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የተደራጀ የምዘና ቡድን በወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የተደራጀ የምዘና ቡድን በወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት በ2017 በጀት ዓመት በአደረጃጀት ዘርፍ የተከናወኑ እቅድ አፈፃፀም ስራዎች ምልከታ እያደረገ ይገኛል ።
በወጣት ክንፍ እቅድ አፈፃፀም ስራዎች ምልከታ እያደረገ ይገኛል ።
በሴት ክንፍ የተከናወኑ እቅድ አፈፃፀም ስራዎች ምልከታ እያደረገ ይገኛል ።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 08 ቀን 2017
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ በወረዳዉ የተከናወኑ ሰዉ ተኮር እና የውስጠ ፓርቲ ስራዎች የሚቃኝ ዓመታዊ መጽሄት አዘጋጅቶ አስመረቀ።
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳዉ የተከናወኑ የሰዉ ተኮር ፕሮጀክት፣ በግብርና፣ በስራ ክህሎት እንዲሁም የኢንሼቲቭ ስራዎች እና ሌሎች በወረዳ ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የተተገበሩ ክንዉኖችን በማስመልከት የወረዳው ፓርቲ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አጠቃላይ ስራዎችን የሚዳስስ የስራ ማጠቃለያ በጀት ዓመቱ አስመልክቶ አመታዊ ቅኝት መጽሄት በማዘጋጀት አስመረቀ።
ሰው ተኮር የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ከሚያከናውናቸው መርሃ ግብር አንዱ በጎነት በሆስፒታል ነው።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ወጣት ክንፍ "በጎነት በሆስፒታል" በሚል መሪ ሀሳብ በአለርት ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት ምግብ ነክ መጠጦችንና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለታካሚዎች ድጋፍ አደረገ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ቤተልሄም ትዳሩ፣ የወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እና የወረዳ 07 ወጣት ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት እታገኝ አምባቸው እና ስራ አስፈፃሚዎች በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል። ወጣት ቤተልሄም ትዳሩ እንደተናገሩት በጎነት በሆስፒታል በሚል መሪ ሀሳብ በህመም ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን መጠየቅ ሲሆን በዛሬው እለት ይህን ተግባር ለማበረታታትና ለመፈጸም በአለርት ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል መገኘታቸውን ገልፀው በበጎ ፍቃድ የሚያከናውነው ተግባር በወንድማማችነትን እና እህትማማችነት መሀከል የመተባበር፣ የመደጋገፍና የአብሮነትን እሴት የሚያሳድግ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል ።
የወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑን ማሳያ የሆነው በጎ ፍቃድ አንዱ ነው በበጎ ፍቃድ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የሆነው የበጎነት በሆስፒታል መርሃ ግብር በህመም ላይ የሚገኙ ታካሚዎች ደጋፊና ጠያቂ እንዳላቸው እንዲረዱ ለማድረግ ያለመ ሲሆን እንደዚህ አይነት መሰል ተግባራት የመደጋገፍ ባህላችን እንደሚያጎለብትም ገልፀዋል ።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 04 ቀን 2017
የስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ ደም በመለገስ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት መታደግ ነው!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡
በዚህ ደም ልገሳ ላይ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ የወረዳው አመራሮች፣ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ደም ለግሰዋል፡፡
የወረዳው የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰዒድ አብዱራህማን ባስተላለፉት መልዕክት ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ለመታደግ ደም መለገስ የስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ ነው ሲሉ ገልጸው
የደም ልገሳው በወሊድ ጊዜ እና በአደጋ ጊዜ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንደሚውል የገለጹ ሲሆን አንድ ሰው የሚለግሰው ደም ለ3 ሰዎች ህይወት መታደግ እንደሚችን ተናግረዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሐምሌ 02 ቀን 2017
ሰው ተኮር የሆነው ብልፅግና ፓርቲ የ90 ቀናት ተግባራትን በማስመልከት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄ
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ በ90 ቀን እቅድ ተይዞላቸዉ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የሰዉ ተኮር ተግባር አንዱ የሆነዉ ማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር በዛሬዉ ዕለት በወረዳዉ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ዉስጥ ተካሄደ፡፡
አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ባደረጉት ንግግር በ90 ቀናት ዉስጥ በእቅድ ተይዘዉ ከሚከናወኑ በርካታ ተግባራት መካከል የሰዉ ተኮር ተግባራት ሲሆኑ እነዚህንም በጎ ተግባራት አጠናክረን በመቀጠል፣ በመደጋገፍ፣ አብሮነታችን አንድነታችን ልናጎለብት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
የወረዳ 07 ህብረተሰብ ተ/በ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰይድ አብድራህማን እንዲሁም ሴቶች ህጻናት ማ/ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኤልሳ ኪዳኔ በጋራ በመሆን ፕሮግራሙን ያስተባበሩ ሲሆን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች፣ አረጋዉያን እና አካል ጉዳተኞች በአይነት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 30 ቀን 2017
ህብረተሰቡን ያሳተፈ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ተካሔደ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ-07 አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት ጀርባ አካባቢ የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እንዲሁም የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮች፣ ደንብ ኦፊሰሮች፣ ባለሙያዎችና ነዋሪዎችን በመርሀ-ግብሩም ላይ ተገኝተው የ2017/18 7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
አቶ ለማ ቱሉ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ በመርሀ- ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የሀገራችንን የአረንጓዴ ሽፋን በማሳደግ ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን፤ በ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በወረዳችን አንድ መቶ ሺ ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጸው እየተተከሉ የሚገኙ ችግኞች መፅደቅ ላይ በትኩረት በመስራት ችግኞችን መንከባከብ እንደሚገባም አሳስበዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 30 ቀን 2017
በዘጠና ቀናት ታቅደው እየተሰሩ ያሉ ተግባራት በአጠቃላይ አመራሩ የጋራ ውይይት ተደረገ
የገቢ አሰባሰብ፣ ጉድጓድ ቁፋሮ ችግኝ ተከላ፣ የደጃፍ መብራት ማስወጣ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ አሰባሰብ እንዲሁም የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ጋር ተያይዞ አጠቃላይ አመራሩ በተገኙበት የጋራ ውይይት ተካሄደ
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እንደተናገሩት የችግኝ ተከላ ጉድጓድ ቁፋሮ በስታንዳርዱ መሰረት ቆፍሮ ዝግጁ በማድረግ ሀገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኞች በማስገዛት ለተከላ ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት ገልጸው የውስጠ ፓርቲ ስራዎች አጠናክረን በመስራት ፓርቲያችን በፋይናንስና በሰው ሀይል ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
አቶ ወ/ሚካኤል አበራ የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት የገቢ አሰባሰብ ስራችን ቤት ለቤት መረጃ ወስዶ ቅስቀሳ በማድረግ የገቢ ግብር አሰባሰብ ስራችን በውጤታማነት ማሳካት አለብን ሲሉ ገልጸዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 29 ቀን 2017
ፓርቲን ለማጠናከር ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ በመሆኑ የዓመቱን ሪፖርት ከወረዳው ም/ቤት ጋር የጋራ ተደረገ
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ከወረዳው ም/ቤት ጋር በመሆን የ2017 በጀት ዓመት የውስጠ ፓርቲ ስራዎች የየዘርፉን ሪፖርት እና የወረዳው የም/ቤቱን ሪፖርት የጋራ ተደርጓል።
የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ኮሚቴ፣ የወረዳው ም/ቤት አፈ-ጉባዔ እና የም/ቤት ፀሐፊ በተገኙበት የውስጠ ፓርቲ ስራዎች የ2017 በጀት ዓመት በየዘርፉ ሪፖርት ቀርቦ ክፍተቶችና ጥንካሬዎችን በማንሳት እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸውን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ግምገማ ተደርገዋል።
ፓርቲያችን ለማጠናከር የተሰሩ ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በ2018 በጀት ዓመት እንዲሸገሩ እና ጥንካሬዎችን ወስዶ ክፍተቶችን በማረም ሁሉም ዘርፍ የፓርቲውን ዓላማ ለማሳካት ተልዕኮዎችን በሚገባ መወጣት እንደሚገባ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ገለፀው ጥንካሬያችንና ድክመቶቻችንን ለይተን በቀጣይ በጀት ዓመት በጋራ ተረባርበን ሁሉም ለተመደበበት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የተሻለ ውጤት ማምጣት ይጠበቅብናል በሚል ሀሳብ ላይ ተግባብተዋል።
አባላትን ማጠናከር ለሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገት እና ብልፅግናን ለማፋጠን ወሳኝ ነው።
በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ብልፅግና ህብረቶች ፣ ብልፅግና ቤተሰቦችና አባላት የወረዳው 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት አመሰገናቸው።
በምስጋና ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ የወረዳ 07 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ እንደገለፁት የብልፅግና አባላት የውስጥ አቅማቸውን በማጠናከርና በመካከላቸው ያለውን ትብብር በማስቀጠል፣ ቅንጅታዊ አሰራርና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና ከፍ ማድረግ የሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግናን ለማፋጠን ወሳኝ ነው ብለዋል።
አባላትን ማጠናከር ለሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገት እና ብልፅግናን ለማፋጠን ወሳኝ ነው።
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት በ2ተኛው መደበኛ ጉባዔ የተሻሻለ መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች መመሪያዎች ለብልፅግና ህብረት አመራሮች፣ የብልፅግና ቤተሰብ አመራርችና አባላት ስልጠና ተሰጠ።
የመተዳደሪያ ደንብ ሰነድ ያቀረቡ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ ተማም፣ የውስጠ ፓርቲ አሰራርና አደረጃጀት መመሪያ ሰነድ ያቀረቡ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፊ ኃላፊ ወ/ሮ ሔርሜላ አሰፋ እንዲሁም የተሻሻለውን የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን መተዳደሪያ ደንብ በወረዳው ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነኢማ አህመድ በመቅረብ ለአባላት ግንዛቤ ተፈጥሯል።
የብልፅግና አባላት በሀገር ግንባታ ስርዓት የማይተካ ሚና እንዳላቸዉ እና ሀገረ መንግስት ለመመስረት የአባላት ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃዉ ያሉ የብልፅግና ህብረት እና ቤተሰብ አመራሮች በየአደረጃጀታቸዉ ጠንክረዉ መዉጣት ከቻሉ እንደ ፓርቲም ሆነው እንደ ሀገር ለመገንባት እየተሠራ ላለዉ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አጋዥና አቅም እንደሚሆን በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ ገልፀዋል ።
ኃላፊው አክለውም የብልፅግና አባላት የውስጥ አቅማቸውን በማጠናከርና በመካከላቸው ያለውን ትብብር በማስቀጠል፣ ቅንጅታዊ አሰራርና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና ከፍ ማድረግ የሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግናን ለማፋጠን ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል።
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አዘጋጅነት "ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት" በሚል መሪ ሀሳብ የፊት ለፊት መድረክ ተካሂዷል።
ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የፊት ለፊት መድረኩ ለሀገር ግንባታ መሠረት የሚጥሉ የገዢ ትርክት ግንባታችን ላይ ማተኮር ይገባናልም ሲሉ ገልፀዋል። ሚዲያ ለገዥ ትርክት ግንባታ ወሳኝነት ያለው በመሆኑ አጠናክሮ መቀጠል አለበት የተባለ ሲሆን አወንታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማተኮር መስራትም እንደሚገባ ተገልጿል።
የክፍለ ከተማው የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል፣ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ፍቃዱ በመድረኩ ተገኝተው የመነሻ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ታላቋን ሀገር ለመገንባት የገዢ ትርክታችንን ለማጽናት በቅድሚያ ከብሔርተኝነት ተላቀን ብሔራዊት ለማስረፅ ዝግጁ መሆን ነው ብለዋል። ብልጽግና ፓርቲ የብሔራዊነት ትርክት እንዲጸና ለማድረግ እና በህዝባችን ዘንድ ያለው ተቀባይነት እንዲጎለብት ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል።
የክፍለ ከተማው የፓርቲ ሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው ወ/ሮ የእናትፋንታ ዘሪሁን በበኩላቸው ሀገርን ለማጽናት ከቀደመው የአድዋ ድል ትምህርት በመውሰድ አባቶቻችን ያጸኗትን ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ የገዢ ትርክት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን ሲሉም ገልፀዋል። የነበረን እሴት ሀገር ለማሳደግና ለማበልጸግ ያስችለናል ያሉት ኃላፊዋ ለትውልድ የምትመች ሀገር ለመፍጠር ልክ እንደ አድዋው ድል የሁለተኛው ዙር ምዕራፍ አርበኝነትን በብሄራዊነት ትርክት በመነሳሳት መሥራት አለብን ብለዋል። የገዢ ትርክትን ለማጽናትም ሚዲያ ያለውን ሚና በመረዳት መሥራት ይኖርብናል ብለዋል።
የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በበኩላቸው የገዢ ትርክት የወል ሀገራችንን ለማጽናት ካለን ልዩነት ይልቅ የጋራ የሚያደርጉን ላይ ማተኮር አለብን። ሀገር እንድትጸና የሚያደርጉ ጉዳዮች ማጉላት ላይ ማተኮርም ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል። አንድ የሚያደርጉን ላይ ማተኮር ድል የሚያስገኝልን በመሆኑ በተገቢው መቆም ይገባልም ብለዋል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎችየተሰጠውን ገለፃ መነሻ በማድረግ ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚሰሩ ገልፀው የገዢ ትርክት ብዝሃነት ባለበት ሀገር ውስጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንዲጸና መስራት ይጠበቅብናል በማለት የገዢ ትርክታችንን በማጠናከር የበለፀገች ሀገር ለመገንባት የጋራ ሃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 12 ቀን 2017
"ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው ባሉ ወረዳዎች የፎቶ አውደርዕይ እና የባህል ሲምፖዚየም ተከናወነ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት ሁሉም ወረዳዎች የተሳተፋበት "ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ከሀገራዊ ለውጡ ጀምሮ የተከናወኑ ስራዎችን የሚዘክር የፎቶ አውደርዕይ እና የባህል ሲምፖዚየም ተካሄዷል።
የተዘጋጀው ሲምፖዚየም በክፍለ ከተማው የሚገኙ 11ዱም ወረዳዎች የተሳተፋ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎችን እና ከለውጡ ጀምሮ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትንና ውጤቶችን በሚያሳይ መልኩ እንዲሁም የተለያዩ የብሄር ብሄረሰብ የባህል ክዋኔዎችን ለእይታ አቅርበዋል።
በዕለቱም አቶ ስዩም ከበደ የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ወንዱ አሰፋ የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ፣ ወ/ሮ ኒእመተላህ ከበደ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አቶ ሙሉጌታ ጉልማ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ እና ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በወረዳዎች የተካሄደውን የፎቶ አውደ ርዕይ እና የባህል ሲፓዚየሙን ተመልክተዋል ።
በብልፅግና ፓርቲ ለባለፋት ሰባት ዓመታት የተሰሩ የብልፅግና ትሩፋቶች በተለያዩ መስኮች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ እና በዲፕሎማሲያዊ የተመዘገቡ ስኬቶች በሚገባ በሚያሳይ መልኩ የተካሄደው አወደ ርዕይና የባህል ሲፓዚየም የኢትዮጵያን የልዕልና ጉዞ በስኬት እየቀጠለ መሆኑ የሚያሳይ እና በወረዳዎች መካከል መልካም ልምዶችን ከመቅሰም በተጨማሪ እህትማማችነትንና ወንድማማችነትን በማጠናከር ለተሻለ ስራ መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላክቷል።
ብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት "ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፊት ለፊት መድረክ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት" በሚል የተዘጋጀ የፊት ለፊት መድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ በወንድማማችነትና እህትማማችነት ላይ የተመሰረተ ህብረብሔራዊነትን የሚያጎለብት የመደመር መንገድን በመከተል ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ብልጽግና ፓርቲ ይህንን በመረዳት ለጠንካራ ሀገረመንግስት ግንባታ እየሰራ መሆኑን ገለፀው ሁሉም ሰው ይህን በአግባቡ በመረዳት የብሄራዊ ገዥ ትርክት በሚገባ ለማህበረሰቡ ለማስረጽ ሀገራዊ ግዴታ አለብን ብለዋል።
የወረዳ 07 አስተዳደር አቶ ለማ ቱሉ በበኩላቸው የወል ሀገርን በወል ዕውነቶች ላይ አጽንቶ ሀገራዊ ልዕልናን ለማብሰር ትርክት ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል። ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት ህዝብን አስተሳስሮ የጋራ አላማ የሚፈጥር ሀገራዊ ገዢ ትርክ መፍጠር ነው በማት የሀገራችን ህዝቦች ለጋራ አላማ አብሮ በመቆም ፣ፍትሀዊነትን ፣እኩልነትን በማረጋገጥ ፣ብዙሃነትን በማክበር የወል ትርክታችንን መገንባት ይገባል ብለዋል ።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 12 ቀን 2017
ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት
ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት
ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት
ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት "ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት" በሚል መሪ መልዕክት የፎቶ አውደ ርዕይ በዛሬዉ እለት ለእይታ ቀርቦ እየተጎበኘ ይገኛል።
ባለፉት 12 ወራት እንደ ወረዳ 07 ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አራቱ ከብልፅግና ፕሮግራሞች አንፃር የተሰሩ ስራዎች፣ ሰዉ ተኮር ተግባራት፤የልማት አበይት ስራዎችንና በብራንዲንግ ሥራ የተከናወኑ ተግባራትን የሚያሳይ የፎቶ ስብስብ ለምልከታ ቀርበው በክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተከፍተው በብልፅግና ፓርቲ አባላት፣ በወረዳዉ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ ባለጉዳዮችና ነዋሪዎች የፎቶ መስኮት አውደርዕዩን ጎብኝተዋል፡፡ የተሰሩ ስራዎችን ከሚዲያ ባሻገር በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች በመጠቀም ስራዎችን እና መረጃዎችን ተደራሽ የተደረገበት ሁኔታና ብልፅግና ፓርቲ እያከናወነ ያለው ተግባራት ይበል የሚያሰኝ መሆኑንና ጉብተኞች አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 12 ቀን 2017
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
ብልፅግና ለትውልድ የሚሰራ ፓርቲ ነው!
የአካባቢን እምቅ አቅም በመጠቀም የሚከናወኑ ተግባራት ለህጻናት እድገት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ተጨማሪ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ECD የክ/ከተማ አስተባባሪ አመራሮች በተገኙበት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
በብልፅግና ፓርቲ ኢኒሼቲቪ ከቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙት የህጻናት መጫወቻ ቦታዎች በየክላስተሩ ተሰርተው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ መሆኑንና ተጨማሪ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ECD በመገንባት ትውልድ ላይ መስራት ተገቢ መሆኑን የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤትኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልማ ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለውም የሚከናወኑት ተግባራት ህጻናት በአካባቢያቸው እንዲጫወቱ እድል የሚፈጥር ና ለነገው የተሻለ ትውልድ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 12 ቀን 2017
ብልፅግና ለትውልድ የሚሰራ ፓርቲ ነው!
ብልፅግና ለትውልድ የሚሰራ ፓርቲ ነው!
ብልፅግና ለትውልድ የሚሰራ ፓርቲ ነው!
ብልፅግና ለትውልድ የሚሰራ ፓርቲ ነው!
በስራ ዕድል ፈጠራ ዜጎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር፣ የገቢ አሰባሰብ እንዲሁም የውስጠ ፓርቲ ስራዎች በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እንደተናገሩት ያሉንን ጸጋዎች አሟጠን በመጠቀም በስራ ዕድል ፈጠራ ዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማድረግ እንደሚገባ ገለፀው ብልጽግና ፓርቲ በሰው ኃይል እና በፋይናንስ በማጠናከር ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።
ከስራ እድል ፈጠራ አንጻር ዕቅዳችን ለማሳካት ሁሉም አመራርና ባለድርሻ አካላት በቁጭት ርብርብ ተደርጎ ዕቅዳችን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት ይኖርብናል ሲሉ የወረዳው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወልደሚካኤል አበራ ተናግረዋል።
የ90 ቀን ስራዎች ማስፈጸሚያ ዕቅድ ከአጠቃላይ አመራሩ ጋር የጋራ ውይይት ተደረገ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር የ90 ቀን ስራዎች ማስፈጸሚያ ዕቅድ ከአጠቃላይ አመራሩ ጋር የጋራ ውይይት ተካሄደ።
የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የከተማ ግብርና ሌማት ትሩፋት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች፣ ትምህርት ለትውልድ፣ የኮሊደር ልማት፣ የሰላም ግንባታ፣ ገቢ አሰባሰብ፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ አገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር፣ የምክክር ኮሚሽን፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፣ የጳጉሜ ቀናቶች ማክበር እንዲሁም የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ዕቅድ
የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወ/ሚካኤል አበራ በኩል ሰነዱ ቀርቦ አጠቃላይ አመራሮች እና የክ/ከተማ ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ በበኩላቸው የ90 ቀናት እቅዶችን ለማሳካት በቅንጅት በመስራት አመራሩ ተግባራቶችን ቆጥሮ በመስጠት እና ቆጥሮ በመቀበል ሁሉም ተግባራትን በውጤማነት መፈጸም እንደሚገባ ገልፀዋል ። አክለውም የ90 ቀን እቅዳችን ለመተግበር ክፍተቶችን ለይቶ ለመሙላት በጥራትና በፍጥነት ጊዜ የለኝም መንፈስ ስራዎች በውጤታማነት አሳክተን የህዝባችን ተጠቃሚነት እና እርካታ ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል። አቶ ሚሊዮን ወንድሙ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ እንደገለጹት ስምሪትን አስተካክሎ እና ተግባራትን አስተሳስሮ በቅንጅት በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት" በሚል መሪ ሀሳብ ማጠቃለያ የኪነጥበብ ምሽት ተካሂዷል።
በመድረኩም ለበጎ ማህበረሰብ አንቂዎች እና ለወረዳው ፓርቲ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰዎች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 12 ቀን 2017
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
"ከብሔርተኝነት ወደ ብሔራዊነት የብልፅግና ገዢ ትርክት"
ኮሪደር ልማታችን የተምሳሌታዊ ብልፅግና ጉዟችን ማሳያ ነው!
በየጊዜው አድማሱን እያሰፋ ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኘው ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞአችን የልማታችንን ብርሃን ፈንጣቂነት አመላካች ነው፡፡
በየአካባቢው የሚገኙ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አቅሞችን በመጠቀም ሁሉንም ዜጋ የልማቱ ፍትሀዊ ተቋዳሽ ለማድረግ ብርቱ ጥረት መደረግ ከጀመረ ሰነባብቷል። በፓርቲያችን እየተተገበረ የሚገኘው አካታች የኢኮኖሚ እሳቤ በሁሉም አካባቢዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊና ተጠቃሚ አያደረገም ይገኛል። መዲናችን አዲስ አበባም በመፍጠርና በመፍጠን ቃልን በተግባር የመተርጎም ባህልን አጎልብታ ተምሳሌትነቷን አስፋታለች።
በተለወጠ አስተሳሰብ ፣ ቀን ከሌት በመትጋት ፣ አሻራን በማሳረፍ ፣ ከትናንት ወረቶች ላይ የዛሬን አኩሪ ድሎች በመደመር የሀገራችንን ልዕልና ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ የተጀመረው ርብርብ ተስፋ ሰጪ ግስጋሴ ላይ ይገኛል። አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በየደረጃው የሚገኘው አመራር ህዝቡን አስተባብሮ እያከናወነ የሚገኘው ርብርብ እንደ ሀገር ብቻም ሳይሆን እንደ አህጉር ሊሰፉ የሚችሉ ተሞክሮዎችን ማስገኘት ጀምሯል ፤ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጭምር የአዲስ አበባን የልማት ሞዴል ወደ ሀገራቸው ለማስፋት እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።
አዲስ እየተገነባ በሚገኘው ጠንካራ የስራ ባህል በአጭር ጊዜ ውስጥ ተተግብሮ ተጨባጭ ስኬትን ያረጋገጠው የከተማችን የመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት ውጤታማ አተገባበር የሀገራችንን ከተሞች የመልማት አቅም መግለጥ ችሏል። ከከተማችን የተጀመረው የዘመናዊ ከተማነት ስታንዳርድን የማስጠበቅ እንቅስቃሴ በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ አቅጣጫ ሰጪነት ወደ ሁሉም ክልሎች እየሰፋ ሲሆን የገጠር ኮሪደርም መተግበር ጀምሯል። እንደ አዲስ አበባ ሁሉ ረጅም ታሪክ ይዘው ስማቸውን በማይገልፅ ግብር ውስጥ የቆዩ በርካታ የሀገራችን ከተሞች በከፍተኛ የልማት መነቃቃት ውስጥ ገብተዋል።
የኮሪደር ልማቱ በሀገር ደረጀ መስፋት የከተሞቻችን ጉስቁልና በማስወገድ የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ እያሻሻለ ይገኛል። በጉልበትም ፣ በገንዘብም ፣ በእውቀትም አብዛኛው የኮሪደር ልማት በራስ አቅም እየተከናወነ ስለሚገኝ ለኮንትራክተሮች እና ለኢንተርፕራይዞች ትልቅ ዕድል የፈጠረ ሲሆን የስራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴውም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስችሏል። የከተማችንን ተምሳሌታዊ የብልፅግና ጉዞ አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝባችንን የዘመናት የልማት እና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት ማርካታ አሁንም ቢሆን አንዳች መዘናጋት የማይፈልግ መሆኑን በመረዳት ለላቀ ድል ይበልጥ መትጋት ይገባል።
ፓርቲን ለማጠናከር ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።
የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ኮሚቴ የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ክፍተቶችና ጥንካሬዎችን በማንሳት እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸውን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ግምገማ አድርገዋል።
የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ የተገመገሙ ሲሆን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ ፓርቲን ለማጠናከር ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ መሆኑ ገለፀው ጥንካሬያችንና ድክመቶችን ለይተን የቀሩ ተግባርቶቻችን ላይ በጋራ ተረባርበን ሁሉም ለተመደበበት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የተሻለ ውጤት ማምጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 09 ቀን 2017
ጠንካራ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን በአቅም ግንባታ ስልጠና በመገንባት ለሁለንተናዊ ተልዕኮ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
በዛሬው እለት የኮልፌ ቀራኒዮ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት ተልዕኮ በብቃት መወጣት በሚል ርዕስ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምሕረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) አመካኝነት ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በስልጠናው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ስልጠናው የአመራሩን አቅም በመገንባት እንዲሁም የበለጠ በማነሳሳት የፓርቲው እና መንግስት ተልዕኮዎች በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
አቶ ሙሉጌታ አያይዘውም አመራሩ በዚህ ስልጠና ያገኘውን ተጨማሪ አቅሞ ይዞ ወደ ስራ በመግባት በ90 ቀናት የተቀመጡ ከ18 በላይ ግቦች ወደ ውጤት በመቀየር ስራዎችን በውጤት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በስልጠናው የተገኙት አቶ ዳዊት ምንዳዬ በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ ባደረጉት ንግግር ኮልፌ በ2017 በጀት አመት በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሰጡት ክፍለ ከተሞች ከፊት የሚገኝ መሆኑን በማስታወስ መሰል ስልጠናዎች የአመራሩን የመምራት አቅም የሚጨምሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስልጠናው የሰጡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምሕረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ሲሆኑ ተልዕኮን በአግባቡ መወጣት በሚል ርዕስ ትኩረት የሚፈልጉ ሀላፊነት መውሰድ፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ የህዝብ ፍላጎት መረዳትና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲሁም ተልእኮን በአግባቡ ለመወጣት ችግር የሚሆኑ በርካታ ፅንሰ ሀሳቦች የመፍትሄ መንገዶች ዙሪያ ዝርዝር ገላፆ አድርገዋል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በመጠየቅ የራሳቸው ሚና እንደሚወጡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ጠንካራ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን በአቅም ግንባታ ስልጠና በመገንባት ለሁለንተናዊ ተልዕኮ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጠንካራ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን በአቅም ግንባታ ስልጠና በመገንባት ለሁለንተናዊ ተልዕኮ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጠንካራ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን በአቅም ግንባታ ስልጠና በመገንባት ለሁለንተናዊ ተልዕኮ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጠንካራ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን በአቅም ግንባታ ስልጠና በመገንባት ለሁለንተናዊ ተልዕኮ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
የ90 ቀናት አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ የቀጣይ ዘጠና ቀናት የንቅናቄ ስራዎች በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት በባለፉት ዘጠኝ ወራት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ በገቢያ ማረጋጋት ፣ገቢ አሰባሰብ ህገ ወጥ ንግድ መከላከል ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት በማካሔድ በቀጣይ 90 ቀናት የሚተገበሩ የንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት ተካሔዷል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ እንዳሉት በሌማት ትሩፋት፣ የመልካም አስተዳደር፣ ኢ ሲ ዲ፣ የወንዞች ዳርቻ ልማት፣ ገቢ አሰባሰብ፣ ከገቢያ ማረጋጋት እቅዶችን ለማሳካት የተደረጉ ጥረቶች እና የተመዘገቡ ውጤት የሚበረታታ ሲሆን ከስራ እድል ፈጠራ አንጻር ዕቅዳችን ለማሳካት ሁሉም አመራርና ባለድርሻ አካላት በቁጭት እርብርብ ተደርጎ ዕቅዳችን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ እንዳሉት ባለፉት 90 ቀናት በእቅድ ተይዘው የተሰሩ በርካታ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ገልጸው በሌማት ትሩፋት ስራዎችን፣ የገቢ አሰባሰብ የገበያ ማረጋጋት፣ የወንዞች ዳርቻ ልማት ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸው የስራ እድል ፈጠራ በትኩረት ይዘን በመስራት ዕቅዳችን ማሳካት ይኖርብናል በማለት ገልጸዋል። በመጨረሻም በቀጣይ 90 ቀናት ውስጥ የሚሰሩ 18 የሚሆኑ ተግባራቶች የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጧ።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ሰኔ 05 ቀን 2017
የ90 ቀናት አፈፃፀም ግምገማ
የ90 ቀናት አፈፃፀም ግምገማ
የ90 ቀናት አፈፃፀም ግምገማ
የ90 ቀናት አፈፃፀም ግምገማ
ብሔራዊነት ዘመኑን የዋጀ ፣ ነገን ታሳቢ ያደረገ ገዢ ትርክት ነው!
ብልፅግና አማካኝ እሳቤን የሚያራምድ ተራማጅ ፓርቲ እንደመሆኑ ከመገፋፋት እና ከፅንፍ አስተሳሰብ ነፃ የሆነው ብሔራዊነት ገዢ ትርክት እንዲሆን ታግሎ ያታግላል።ብሔራዊነት ማለት ህገ መንግስታዊነትን መሰረት ያደረገ ኅብረብሔራዊ አንድነት ማለት ነው።
ብሔራዊነት ከዋልታ ረገጥነት እሳቤ የራቀ በመሆኑ ለአስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላማችን እንዲሁም ፍትሀዊ ዕድገታችን ትክክለኛውን ገዢ ትርክት መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል።
የሀገራችን የመተሳሰብ የመረዳዳት እና የአብሮነት ነባር እሴቶች ከፍ እንዲሉ ፓርቲያችን የጀማመራቸው ብርቱ ጥረቶችም ለሁሉም እኩል ዕድል የሚሰጥው ብሔራዊነት እንዲጎመራ ድርሻቸው ከፍ ያለ ነው።
ሲንከባለሉ የመጡ እና አዳዲስ የተፈጠሩ የነጠላ ትርክት ዕዳዎቻችን እልባት የሚያገኙት ጫፍ እና ጫፍ ቆመን በመጠላለፍ ሳይሆን የግልን እና የቡድንን ፍላጎት ለጋራ ሀገራዊ ዓላማ በማስገንዘብ በመሆኑ ሀገራዊ መግባባት ዕውን ለማድረግ ለጀመርነው ጥረትም የብሔራዊነት ገዢ ትርክትን ለመገንባት አጥብቀን መሻታችን የፓርቲያችን የጠራ አቅጣጫ ነፀብራቅ ነው።
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለ1ሺ 446ኛዉ የዒድ አል አደሃ (አረፋ ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ
የኮልፌ ቀራንዮ የወረዳ 07 አስተባባሪ ኮሚቴ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አስተላልፏል።
የአረፋ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ፣ ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ ትርጉሙና ፋይዳዉ እጅግ ከፍተኛ ነዉ።
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የፈጣሪ ትዕዛዛትን የመቀበልና የመተግባር የፈጣሪ ትዕዛዛቱ የመገዛትና የመሰዋት ሃይማኖታዊ አሰተምህሮ አብነት ተደርጎ ይወሰዳል።
በአረፋ በዓል ከራስ አልፎ ለሌሎች የመድረስና የመለገስ ማህበራዊ አስተምህሮ እንደ አንድ የበዓሉ አካል ተደርጎ ይወሰዳል ።
የአረፋ በዓል ፣ በገንዘብ እጥረት፣ በጤና እክልና በሌሎችም ምክንያቶች ለተቸገሩ ወገኖች መድረስ ግዴታ ተደርጎ የሚወሰድበት፣ ተካፍሎ የመብላት ማህበራዊ እሴት ጎልቶ የሚታይበት ነዉ።
ስለሆነም እነዚህን የበዓሉን ሃይማኖታዊና ማህበራዊ እሴቶች በማጠናከር የመረዳዳትና የመተባበር ባህልን ማጎልበትና በጎነትን ማጠናከር የዘወትር ተግባራችን እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።
መልካም የዒድ አል አደሃ ( አረፋ ) በዓል!
የኮልፌ ቀራንዮ የወረዳ 07 አስተባባሪ ኮሚቴ
"ልምድ ልውውጥ በማካሄድ ፣ ምርጥ ተሞክሮዎች በማስፍት የተቋም ግንባታ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን !!" አቶ ለማ ቱሉ ፈይሳ - በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈፃሚ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር አመራሮች በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር በመገኝት የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።
በልምድ ልውውጡ በወረዳው አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ፣ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር የተሰሩ የቢሮ እና የምድረ ጊቢ የማስዋብ ስራዎች፣ አገልግሎትን ለማዘመን የተሰሩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በተጨማሪም በወረዳ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ያካተተ ነው።
አቶ ሁሴን ቢሉ የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ በወረዳው የተከናወኑ ስራዎችን ያስጎበኙ ሲሆን ተግባራቱም በክፍለ ከተማው ድጋፍ፣ በወረዳው አጠቃላይ አመራር እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የወሰዳችሁትን ልምድ በማስፋትና ያላችሁን ከዚህ በበለጠ በመጠቀም ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቃል ሲሉ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል።
በወረዳው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰው ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ምድረ ግቢ ግንባታ ፣አጠቃላይ የሪፎርም ተግባራትን እና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዴት እያከናወኑ እንደሚገኙና ለየት ያሉ የአሰራር ሂደቶችን የሚያሳይ ተግባራት በመስክ ምልከታና ልምድ ልውውጥ ተደርጓል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ግንቦት 11 ቀን 2017
ልምድ ልውውጥ
ልምድ ልውውጥ
ልምድ ልውውጥ
ልምድ ልውውጥ
"የከተማ ግብርና ለምግብ ዋስትና ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ተካሂደ።
በፕሮግራሙ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ፣ የኮልፌ ቀ/ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቆያ ላሌ እንዲሁም የወረዳ አመራሮችና ከየ ብሎኩ የተወጣጡ ነዋሪዎች በተገኙበት "የከተማ ግብርና ለምግብ ዋስትና ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ተካሂደ።
አቶ ለማ ቱሉ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት የሌማት ትሩፋት ስራዎች ባለችን ቦታ በዶሮ እርባታ፣ በጓሮ አትክልት፣ በወተት ከብት እርባታ እንዲሁም በንብ ማነብ ስራ ላይ ተሰማርተን ምርት ምርታ ማነት በማሳደግ የኑሮ ውድነት ለማቃለል መሰረታዊ ተግባር ነው በማለት ገልጸው ዶሮ በማርባት ልጆቻቹ እንቁላል በመመገብ ጤናማና በአስተሳሰባቸው የላቁና የበለጸጉ ትውልድ በማፍራት እንዲሁም የእንቁላል ዋጋ እንዲቀንስ በማድረግ እና ፍሬሽ ምግብ ከጓሮ አምርተን መመገብ መቻል ይኖርብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፏል።
https://www.kolfekeranyoworeda07prosperity.gov.et/ዋና-ገጽ
ግንቦት 09 ቀን 2017
የሌማት ትሩፋት
የሌማት ትሩፋት
የሌማት ትሩፋት
የሌማት ትሩፋት
እንኳን ደስ አላችሁ!
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አዘጋጅነት ከብልፅግና ህብረት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የጥያቄና መልስ ውድድር በዛሬው ዕለት በተካሄደው የማጠቃለያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ላይ *ወረዳ 07 1ኛ ደረጃን* በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኖዋል።
በኮልፌ ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊና ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ ተማም የእንኳን ደስ አለን መልዕክት በማስተላለፍ በከተማ ደረጃ ለሚካሄደዉ ጥያቄና መልስ ዉድድር ክ/ከተማችን ወክለው ተሳታፊ መሆናቸውን አክሎበታል።
የጥያቄና መልስ ውድድር
የጥያቄና መልስ ውድድር
የጥያቄና መልስ ውድድር
የጥያቄና መልስ ውድድር
ተግባራቶች በውጤት በመስራት የዜጎች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች እና የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ECD፣ የውስጠ ፓርቲ ስራዎች እንዲሁም የኦ.ል.ማ እና የገቢ አሰባሰብ የተሰሩ ስራዎች በመገምገም የቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች አቅጣጫ አስቀምጧል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች እና የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ECD፣ የውስጠ ፓርቲ ስራዎች እንዲሁም የኦ.ል.ማ እና የገቢ አሰባሰብ የተሰሩ ስራዎች በመገምገም የቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች አቅጣጫ አስቀምጧል።
የወረዳው ዋና አስፈጻሚ አቶ ለማ ቱሉ እንደገለጹት አቅማችንና ጊዜያችን በአግባቡ ተጠቅመን አደረጃጀቶች በማሳተፍ፣ ስራዎች አስተሳስሮ በመተግበር የስራ ዕድል ፈጠራ ስራ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት፣ ያሉን ጸጋዎች በአግባቡ አሟጠን በመጠቀም የወጣቶችና ሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።
አክለውም ከተማ ውበት አረንጓዴ ልማት ህብረተሰቡ በማስተባበር እየለሙ ያሉትን በማስቀጠል እና ያልተጀመሩ ECD ግሪነሪዎች ወደ ተግባር በማስገባት በአጭር ጊዜ አልምቶ በማጠናቀቅ ለህጻናት መጫወቻና መዝናኛ ክፍት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል አያይዘውም ማዘጋጃቤታዊ ገቢ አሰባሰብ የተሻለ ስራ ለመሰራት እንዲያስችል ያልተሰበሰበ ገቢ እንዲሰበሰብ በማድረግ ዕቅዳችን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት ይኖርብናል በማለት ገልጸዋል።
በብልጽግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በበኩላቸው የስራ ዕድል ፈጠራ ስራችን የመጡ ለውጦች በማስቀጠል ያልሰራናቸው ተግባራቶች ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የተሰጠንን ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኃላፊው አክሎም በየብሎኩ ስራ ፈላጊ፣ ጸጋ ልየታ እንዲሁም የስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች አስተሳስረን በመስራት ቅድሚያ ለሚሰጡ ተግባራት ፈጥነን በመተግበር ውጤታማነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ አዘጋጅነት በወረዳው የሚገኙ ሞዴል ብልፅግና ህብረት ተቋማት መካከል ውድድር ተካሄደ።
በፕሮግራሙ ላይ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በመድረኩ ተገኝተው በዘንድሮ በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የሰራናቸውን ስራዎች በብልፅግና ህብረት ደረጃ ጠምሮ በማዘጋጀት በመወዳደር ፓርቲያችን የያዘውን ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን በማጠናከር እንዲሁም የዛሬው ውድድር በተግባራት ላይ ብልፅግና ህብረቱ ተሞክሮዎችን እያዳበረበት መሆን ይገባል በማለት አንስተዋል።
የወረዳው የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሔርሜላ አሰፋ በበኩላቸው ውድድሩ የብልፅግና ህብረት ተቋማትን የተሞክሮ እና የልምድ ልውውጥ መፍጠሪያ መድረክ በመሆኑ እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች ተጠናክረው ይቀጥላሉ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ውድድሩንም:-
1ኛ የቀጠና 2 መኖርያ ብልፅግና ህብረት
2ኛ የትምህርት ቤት ብልፅግና ህብረት
3ኛ የቀጠና 2 ሴት ክንፍ ብልፅግና ህብረት እና የቀጠና 1 ወጣት ክንፍ ብልፅግና ህብረት በመውጣት ውድድሩን ጨርሰዋል።
በመጨረሻም ውድድሩን ደረጃ ውስጥ ገብተው ለጨረሱ ማህበራዊ መሰረቶች ሽልማት እና ዕውቅና በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
ሀገራዊ ገዥ ትርክት በመፍጠር አብሮነታችንን ማጠናከርና አገራችንን መገንባት የሁላችንም ሃላፊነት ነው!
አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በስልጠናው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከለውጡ ወዲህ በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኙ ገልፀው ከዚህ በፊት የነበሩ ስብራቶች ለመጠገን እና የሀገራችን ሁሉን አቀፍ ብልፅግና መረጋገጥ የገዥ ትርክት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ሙሉጌታ አክለውም ብልፅግና ፓርቲ ዜጎች አሰባሳቢ ገዢ ትርክትን በመረዳት በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠርና የድርሻን እንዲወጡ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ስልጠናው የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ምክትል ሀላፊ አቶ ጀማል መሀመድ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በዋናነትም በአብሮነት፣ ስነ ምግባር፣ የትርክት ተረክና ታሪክ ምንነት፣ የገዥ ትርክት፣ ብሔራዊነትና ዐርበኝነት በሚሉ ፅንሰ ሀሳቦች ዙሪያ ዝርዝር ገላፆ ተደረገላቸው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
አቶ አለማየሁ ፍቃዱ ብልፅግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ እንደገለፁት ሁሉም ነገር የትርክት ውጤት በመሆኑ ሀገርን ለመገንባት አሰባሳቢ ገዥ ትርክት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው የሀገርን ብልፅግና ለማረጋገጥ በትብብርና በአንድነት ሁሉም የድርሻውን አሻራ ማኖር አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ብልፅግና በማረጋገጥ ሂደት ላይ የጤና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ፓርቲያችን ብልፅግናም በጤናው ዘርፍ እየመጣ ያለውን እድገት ለማፋጠን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል የብሄራዊነት ገዢ ትርክትን የወል ትርክታችን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል በተለይም የጤና ባለሞያዎች በህብረተሰባችን መሃል እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆናቸው ለዚህ እሳቤ መስረፅ የራሳቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል።
ጠንካራ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ፤ ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ!
ጠንካራ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሲባል ለህግ የበላይነት መቆም፣ ሰብአዊ መብትና መሰረታዊ ነፃነቶች መከበር፣ ግልፀኝነት ተጠያቂነት ፣ለብዘሃነት እውቅና መስጠትና መብት ማክበር፣ የራስን ፍላጎት በነፃነት መግለፅና የሌሎችን ሃሳብ ለማዳመጥ ክፍት መሆን፣ ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እኩል ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ያካተተ ነው።
ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የፓለቲካ አውዳችን ከፉክክር ባሻገር ትብብርን እንዲያካትት፣ ከመገፋፋት ይልቅ እርስ በእርስ ተደጋግፎ ችግርን በጋራ የማለፍ ልምድን እንዲያዳብር ማድረግ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።
ከመናናቅ ይልቅ መከባበር ፣ ከእኔ ይልቅ እኛ ማለትን ፤ የአንዳንችን የሁላችን መሆኑን መረዳትን፣ ከጥላቻ እና ቂም በቀል ይልቅ እርቅና ይቅር ባይነትን ገንዘብ ማድረግ ተገቢ ነው። እነዚህን ወርቃማ የአስተሳሰብ ከፍታ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁላችንም የበኩላችንን ልናበረክት ይገባል። መልዕክታችን ነው።
''ብሄራዊነትን በማስረፅ አስተማማኝ ሀገረ መንግስት የመገንባት ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የስቪክ ማህበራት ሚና የጎላ ነው!!"
ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በተዛባ በፓለቲካ አካሄድ ምክንያት ወደ ተፈለገው ብልጽግና ማማ ሳትጓዝ ቆይታለች ያሉት ብልጽግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ ፥ እንደ ሀገር የነበሩ ችግሮችን በጋራና በውይይት ከመፍታት ይልቅ በመገፋፋትና ከፋፋይ በሆነ ስርዓት በመኖሩ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና ማህበራዊና ቀውሶች እንነበሩ ታሪክ ያሳየናል፤ ኅብረ ብሔራዊነትን፣ አካታችነትን ፍትሀዊነትን እና እኩልነትን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚያረጋግጥ አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ሀገራችን ያስፈልጋታል ብሎ ብልፅግና ፓርቲ ያምናል ያሉ ሲሆን፥ በመሆኑም ፓርቲያችን ብልጽግና ይህንን ለማስቀረት ባለፉት አመታት የነበሩ የፖለቲካ ስብራቶች በመጠገን ሁሉንም አካታችና አቃፊ የሆነ የፖለቲካ ስርዓት በመዘርጋት እንዲሁም አሰባሳቢ ገዢ ትርክት በመገንባት ኢትዮጵያን በሁለም ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የስቪክ ማህበራት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ም/ል እና ፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ፍቃዱ ሲቪክ ማህበራት ለሀገረ መንግስት እና ለብሔረ መንግስት ግንባታ እንዲሁም ለአንድ ሀገር ፓለቲካ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል ስልጠናው ስለ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ስለ ዴሞክራሲ ባህል ልምምድ፣ ስለ ሲቪክ ማህበራት ሚና፣ ስለ ዘላቂ ሰላምና እድገት የሚገባቸውን ሚና እንዲወጡ የሚያግዝ መሆነንም አብራርተዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት 'ብሄራዊነትን በማስረፅ አስተማማኝ ሀገረ መንግስት የመገንባት ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የስቪክ ማህበራት ሚና!' በሚል መሪቃል በሀገረ መንግስት ግንባታ እና በዴሞክራሲ ባህል መዳበር ዙሪያ ለሲቪክ ማህበራት አመራሮች ለስኬታማነቱ ሚናቸውን መወጣት የሚያስችላቸው ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናውን የሰጡት ብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ እንደገለፁት ሲቪክ ማህበራት ለሀገረ መንግስት ግንባታና ለዴሞክራሲ ባህል መዳበር የማይተካ ሚና እንዳላቸው በመረዳት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ሞርካ ኢትዮጵያ ሀገራችን ትናንት ሀገራዊ አንድነትን ለማስጠበቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዋጋ የከፈሉላት፣ ህዝቦቿ ብዙ የተድላ እና የፈተና ጊዜያትን በጋራ ወጥተው የወረዱባት፣ በአንድነትም በልዩነትም ትርክት የተነሳ ግጭት እና ፈተናዎችን ያሳለፈች ሀገር ናት።
ስለሆነም የስቪክ ማህበራት የብልጽግና አርበኝነትን በመላበስ አሰባሳቢ ገዢ ትርክት በመገንባት የበኩላችሁን ሚና እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአፍሪካ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል የፓን-አፍሪካኒዝም እና የአፍሪካ አንድነት ምልክት ነው!!
የአፍሪካ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል በአዲስ አበባ የተገነባው ላለው የፓን-አፍሪካኒዝም እና የአፍሪካ አንድነት ምልክት ነው። ይህ ማዕከል የአፍሪካ ህብረት (AU) ዋና መስሪያ ቤት እና የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች፣ እና የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች የሚገናኙበት ቦታ ነው። ይህ ማዕከል የአፍሪካን የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ ከሚደረገው እንቅስቃሴ አንፃር ትልቅ ትርጉም አለው።
የዚህ ማዕከል የአፍሪካን አገራት በአንድነት እና ትብብር እንዲሰሩ የሚያስችል የአፍሪካን ኩረት በማሳደግ የአፍሪካን ታሪክ እና ባህል ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ የሚያስችል እና የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ማዕከል ነው።
የአፍሪካ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል የአፍሪካን አገራት አንድነት እና ትብብር ምልክት በመሆን የአፍሪካን አገራት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አቅም ለማሳደግ የሚያስችል መድረክ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካን አገራት መሪ እንደመሆኗ ይህ ማዕከል የአዲስ አበባን ኢኮኖሚያዊ ዋና የቱሪዝም እድገት ለማሳደግ የሚያስችል ነው።
ዓድዋ:- ለሁለተኛዉ የኢትዮጵያ አርበኝነት ምዕራፍ መሰረት የጣለ ድል!
ለአሁኑ የኢትዮጵያ ትዉልድ ሁለተኛዉ የአርበኝነት ምዕራፍ የብሄራዊነት ትርክትን በመትከልና በማጽናት የኢትዮጵያን እንድነት በጽኑ መሰረት ላይ ማኖር ነዉ፡፡ የዓድዋ ድልን በትክክለኛ ይዘቱ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ማስተላለፍ መቻል ደግሞ ለዚህ ራዕይ እዉንነት ሊያገለግሉ ከሚችሉ ወሳኝ መሰረታዊያን መካከል አንዱና ወሳኙ ነዉ፡፡ አድዋ የእዉነተኛ ህብረ-ብሄራዊነት መገለጫ ነዉ፡፡ ዓድዋ ከጊዜያዊ ፍላጎቶች በመሻገር ለዘላቂ ሀገራዊ ድል እዉንነት ድርና ማግ ሆኖ የመቆም፣ የአርቆ አሳቢነት አብነት ነዉ፡፡ ዓድዋ የእዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት አርማ ነዉ፡፡
የዚህ ትዉልድ ዓድዋ ከብሄር፣ ከሀይማኖትና ፖለቲካ ጽንፈኝነት በመሻገር ነጻነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መገንባት መቻል ነዉ፡፡ ለዚህ እዉንነት ያለን አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነዉ፡፡ እሱም ቀደም ሲል በሀገራችን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ተሞክረዉ ያላዋጡትን የቀኝና የግራ ፖለቲካ ጽንፈኝነትን በአግባቡ በመግራትና በማረቅ አሰባሳቢ የብሄራዊነት ትርክትን መትከልና ማጽናት ነዉ፡፡
በዉኑ ብሄራዊነት ምንድነዉ? ብሄራዊነት መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት (National Consensus) በመፍጠር በመከባበርና በመተባበር አብሮ የመኖር፣ በተናጠል ማንነቶችና በሀገራዊ ማንነት መካከል ሚዛን ጠብቆ ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምንና ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዳይ ነዉ፡፡
ብሄራዊነት ፓርቲያችን ብልጽግና ገና ከመመስረቱ ጀምሮ ኅብረ ብሔራዊነት፣ አካታችነት፣ ፍትሐዊነት እና እኩልነት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ህልዉና የሚያስፈልጉ መሆናቸዉን በየሰነዶቹ ያረጋገጠዉን በተግባር በማጽናት ኢትዮጵያን ከፍጹማዊ አንድነትና ፍጹማዊ ልዩነት ሰለባነት በመታደግ ዘላቂና ቅቡልነት ያለዉን ሀገረ-መንግስት በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ያነገበው አሰባሳቢ ትርክት ነዉ፡፡
ብሔራዊነት የህዝቦችን የጋራ ጉዳይ ማጉላት ነው፡፡ ብሔራዊነት በአንድነት የሚፀና ብዝኃነት ነው፡፡ ብሄራዊነት በብዝኃነት የሚዋብ አንድነት ነው፡፡ ብሄራዊነት ኢትዮጵያውያን የቋንቋ፣ ባህል፣ ራስን በራስ ማስተዳደር እና ሌሎችም ፍላጎቶች በነጻነት እንዲተገብሩ እኩል ዕውቅና ይሰጣል፡፡ ብሄራዊነት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው የሚያስችል እሳቤ ነው፡፡
የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ የተገመገሙ ሲሆን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ ፓርቲን ለማጠናከር ሥራዎችን በየጊዜዉ መገምገም አስፈላጊ መሆኑ ገለፀው ጥንካሬያችንና ድክመቶችን ለይተን የቀሩ ተግባርቶቻችን ላይ በጋራ ተረባርበን ሁሉም ለተመደበበት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የተሻለ ውጤት ማምጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ኮሚቴ የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ክፍተቶችና ጥንካሬዎችን በማንሳት እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸውን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ግምገማ አድርገዋል።
የአቶ ሞገስ ባልቻ መልእክት...!!
በዛሬው ዕለት "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሃሳብ በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ በመዲናችን አዲስ አበባ አካሂደናል። የፓርያችን የመጀመሪያ ጉባኤ ውሳኔዎችን ለማሳካት በተደረጉ ጥረቶች ሃሳብ በቃል ተነግሮ፤ ቃል ወደ ተግባር ተቀይሮ አይቀሬው የሀገራችን ብልጽግና በከተማችን አዲስ አበባ በፓለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስክ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በተጨባጭ በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ እጅግ አበረታች ውጤቶች ተመዝገበዋል።
የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው። ለዚህም ስኬት ፓርቲው የተናገረውን በመፈፀም በእውነትና በእውቀት እየመራ ይገኛል። አዲስ አበባ ከተማችን ለዚህ ማሳያ ናት። ሀገርን ወደ ብልጽግና ከፍታ ለማሻገር እንዲቻል "'ከቃል እስከ ባህል'' በሚል መሪ ሃሳብ በ2ኛው የፓርቲ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫና ውሳኔዎች እንዲሁም ከነዋሪዎቻችን በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የጋራ ተግባቦት ፈጥረናል። ተደምረን የሁለተኛ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን እውን እናደርጋለን!!
"ብሔራዊነት" የብልፅግና ወርቃማው ትርክት!
ትርክቶች የትናንት ታሪኮችን እንደ እርሾ በመጠቀም ዛሬ ላይ ለምንፈልገው አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ፍላጎቶቻችን የምንጠቀምባቸው፣ፍላጎቶችን የምናሰባስብባቸው መሳሪያዎች ናቸው። ትርክት ተቀባይነት የሚኖረው ስለ ማህበረሰቡ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ግልፅ በሆነ የጊዜና የድርጊት ፍሰት ሲቀርብ፣ድርጊቱ ደግሞ ትርጉም ባለው ሁኔታ መቀመጥ ሲችል ነው። ትርክት የአብሮነት መሰረት ነው!! ሰዎችን ከየት እንደተነሱ እና ወዴት እንደሚደርሱ የሚያመለክታቸው ትርክት ነው። አዎንታዊ ትርክት በህዝብ ውስጥ መነሳሳትን አብሮነትን እና አንድነትን የሚፈጥር የሀገር ታሪክ የወደፊት ተስፋዋን እና ዛሬ ላይ የሚኖረውን ሚና እና የሚከሰቱ ክስተቶችን የምንመለከትበት መነፅር ነው።
ፓርቲያችን እንደ ሀገር "ብሔራዊነት" አዎንታዊ የሆነ ትርክት እንደሆነ በማመን የሀገራችን ገዢ ትርክት እንዲሆን በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። "ብሔራዊነት" ማለት ህገ መንግስታዊነትን መሰረት ያደረገ ኃብረ ብሔራዊ አንድነት ማለት ነው። ህገ መንግስታዊነት ማለት ደግሞ ህዝቦች ተግባብተውና ተስማምተው በህገ መንግስታቸው ላይ ባስቀመጧቸው እሴቶች መሰረት ሀገረ መንግስቱን ለመገንባት መቻል ነው። ህብረ ብሔራዊ አንድነት ማለት ደግሞ የኢትዮጵያውያንን የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሀይማኖት፣ የፆታ፣ የአስተሳሰብ፣ የታሪክ ብዝሀነትን እንደ ጌጥ እንደ ፀጋ የሚቀበል፣ እነዚህን ማንነቶች አስተሳስሮ፣ አስተባብሮ የያዘ ሀገራዊ አንድነት አለ ብሎ የሚያምን ነው። ብዝሀነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው፣ አንድነቱም ብዝሀነቱን ሳይጠቀልለው ብዝሀነቱ ፀጋ፣ ጌጥ አንድነቱም ኋይል ብርታት እንደሆነ የሚቀበል ነው። ብልፅግና ብሔራዊነት ገዢ ትርክቱ እንዲሆን የፈለገበት ምክንያትም አማካይ በመሆኑ፣ በጋራ ነገሮቻችን ላይ ስለሚያተኩር፣ለሁሉም እኩል እድል ስለሚሰጥ እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን ማምጣት የሚችል በመሆኑ ነው፡፡
የፓርቲውን የመጀመሪያ ጉባኤ ውሳኔዎች ለማሳካት በተደረጉ ጥረቶች ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ተመዝግበዋል!!
ብልጽግና ፓርቲ በመጀመሪያ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለማሳካት በተደረጉ ሥራዎች የተሻሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል። :- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በብልፅግና 2ኛ መደበኛ ጉባዔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከመንግስት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በውይይታቸው በጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቀነስ እና ብልሹ አሰራርን ለማጥፋት እንዲሁም የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት ግዴታቸውን እንደሚወጡና መንግስትና ህዝብን ለማገልገል ከምንም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆናቸውን፤ ለሚፈልገው ሁለንተናዊ ለውጥ መሻት አስተዋጽኦ እንዲኖረው ለማድረግ እንደሚሰሩ በውይይታቸው ወቅት አንስተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ''የወል ትርክታችን ለነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ!'' በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት መድረክ አካሄደ።
ከነጠላ ትርክት ወጥተን የወል ትርክት ላይ በትኩረት በመሰራት፤ የበለጸገች ኢትዮጽያ ለመገንባት አሰባሳቢ ገዥ ትርክትን ማስረጽ ይገባል።
ወ/ሮ የእናትፋንታ ዘሪሁን - በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
ብልጽግና ፓርቲ የመሀል ፓለቲካ እሳቤን የሚከተል ተራማጅ ፓርቲ ከመገፋፋት እና ከጽንፍ አስተሳሰብ ነፃ የሆነው ብሔራዊነት ገዥ ትርክት ለማስረጽ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ገዥ ትርክት የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት በመገንባት የነጠላ ትርክት በማጥፋት የወል ትርክትን በማጽናት የጋራ የሚያደርጉንን ጉዳዮች ላይ ልንሰራ ይገባል።
በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አመታት የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ሀገራችን ኢትዮጽያ ወደ ከፍታ ለማምጣት ገዥ ትርክት በማስረፅ የመደመር ሀሳብ በመንደፍ ለቀጣይ ትውልድ የምትመች ሀገር ለመፍጠር ገዥ ትርክትን ለነገ አስተሳሳሪ ትርክት ላይ ልንሰራ እንደሚገባና ከነጠላ ትርክት ወጥተን የወል ትረክት በመገንባት ለነገ ትውልድ የምትሆን ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ለበርካታ ዘመናት የአፍሪካ ህዝቦች ነፃነት ፋና ወጊ መሆኗን እየተገለፀላት ዛሬም ያለችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከህብረቱ ምስረታ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በግንባር ቀደምትነት በተሻለ መንገድ እየተጓዘች ትገኛለች ዛሬም በሀገር ልጆች እውቀት የተጀመረውን የመደመር መንገድ ለሁለንተናዊ ብልፅግናዋ መሰረት ሆኗል ። ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔን በመተግበር የታየው የሰላም መንገድ ያስገኘውን ሰላም ለሌሎች በተምሳሌትነት ከማሳየት በተጨማሪም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን አስጠብቆ የዓለምን ትኩረት በዲፕሎማሲያዊ እቅሟ ታግዛ መሳብ ችላለች ።
በኢኮኖሚያዊ ሪፎርም ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ፣ በቱሪስት መዳረሻነት በኮሪደር ልማት ውብ ሳቢና ማራኪ የከተሞች እድገት ታጅባ በልጆቿ የደመቀ ጉባኤ በማድረግ ለማድረግ ሙሉ ዝግጅቷን አጠናቃ ትገኛለች ። በሀገራዊ ምክክር የትኛውንም የውስጥ ችግሯን እንምትፈታ በጅምር እያሳየች ያለችው ሀገራችን በተጠናከረ የመሪነት ጥበብ የተጀመረውን ድንቅ ጉዞ ጀምሮ ለቀጠናዊ አህጉራዊ ስኬት የምትተጋ ኢትዮጵያ ድንቅ ጉባኤ በስኬት ታካሂዳለች ።
አዲስ አበባ እና አዳዲስ ውብ ገፅታዎቿ!!
Fuulota haaraa Hawwata Finfinnee!!
The new face of Addis Ababa!!
This is Addis Ababa, Ethiopia
አዲስ አበባ እና አዳዲስ ውብ ገፅታዎቿ!!
Fuulota haaraa Hawwata Finfinnee!!
The new face of Addis Ababa!!
This is Addis Ababa, Ethiopia
አዲስ አበባ እና አዳዲስ ውብ ገፅታዎቿ!!
Fuulota haaraa Hawwata Finfinnee!!
The new face of Addis Ababa!!
This is Addis Ababa, Ethiopia
Welcome, our cherished African brothers and sisters, to your home; a place where unity, warmth, and boundless hospitality embrace you! This week, the vibrant and historic city of Addis Ababa will host the 38th African Union Summit, a momentous gathering that unites the leaders of our beloved continent. This extraordinary event symbolizes another milestone in our shared journey of growth, collaboration, and unity.
Addis Ababa, often called the "New Flower," has blossomed into a thriving center of diplomacy, culture, and opportunity. Like the morning sun that illuminates the world, our city shines as a beacon of progress. From its lively streets to its dynamic industries, Addis Ababa is carving out its place on the global stage, emerging as a city of hope, innovation, and limitless potential. This summit is more than just an event; it is a celebration of the resilience and determination of our people. As the eyes of Africa and the world turn to Addis, we have a unique opportunity to showcase the warmth and hospitality that define our city and nation. Our residents, from all walks of life, have always welcomed visitors with open hearts, and this occasion will be no exception.
The presence of our African brothers and sisters here is a powerful reminder of our shared history, collective struggles, and common dreams for a brighter future. It is a time to reflect, to build new partnerships, and to strengthen the bonds that unite us as one continent. As we welcome Africa’s leaders to our city, let us also embrace the responsibility to showcase what Addis Ababa represents, a city of peace, progress, and unity. Let us demonstrate to the world that Addis, with its rich heritage and promising future, is ready to claim its place in the global arena.
From the heart of Africa, we welcome you home. Addis Ababa is where your spirit finds solace and your aspirations soar to new heights!!
➡️ ምሉዕ እይታ/Synoptic፦ አንድ ነገር ብቻ ነጥሎ ከመመልከት ይልቅ የነገሮችን ግንኙነትና መስተጋብር ሳይስቱ በመመልከት ለጭማሬያዊ ውጤት ይጠቁማል።
➡️ መሰናኘት/Synergy/Synchronization፦ ህብረት ከንዑሳን አጠቃላይ ድምር ይበልጣል።
➡️ አስተፃምሮ/Synthesis፦ መደመር የሚተጋው በስርዓት ውስጥ ተደምሮ የሚገኘው ውጤት እያንዳንዱ በግሉ ከሚያበረክተው በልጦ እንዲገኝ ነው።
➡️ ተባብሮ ኑሮ/Symbiosis፦ ተደማሪዎች ምንም ጉዳት ሳያስተናግዱ የሚያተርፉበት ግንኙነት መፍጠር፣የጋራ ግብ አስቀምጦ መንቀሳቀስ።
➡️ ሥርዓት/System፦ የምሉዕ እይታ፣መሰናኘት፣አስተፃምሮ፣ ተባብሮ ኑሮ እና ሚዛን መጠበቅ ድምር ውጤት ነው።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ለትምህርት ቤት መሰረታዊ ድርጅት አባላት በአሰራር በአደረጃጀት እንዲሁም የዲሲፕሊን መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
አባላት የአቅምና የክህሎት በማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት ጠንካራ አባል፤ ለጠንካራ ፓርቲ፤ ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት አባላትን በስልጠና ማብቃት ዋነኛው መንገድ ነው ሲሉ በቀጣይ የተሻለ ስራ መሠራት ይጠበቅብናል በማለት የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊና ፖለቲካ ዘርፊ ኃላፊ አቶ አብድልባሲጥ ተማም ገልጸዋል።
ብልጽግና የተግባር ፓርቲ ፤ ቃል መግባት ሰርቶ ማሳየት ባህሉ ያደረገ !!
ቃል በማክበር በስኬት መገስገስ የኢትዮጵያን ከፍታ ያረጋግጣል! ለለፉት አመታት ፓርቲያችን ብልጽግና ከቃል እስከ ባህል በስኬት የተጓዘበት የኢትዮጵያን የመበልፀግ ተስፋ በተጨባጭ ያሳየ ወቅት ነው። በለውጡ ሂደት በሁሉም መስክ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችሉ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመለወጥ ለዜጎች የምትመችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል። ባለፉት ጊዚያት የሥራ አጥነት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የፕሮጀክቶች መጓተት ወዘተ ይታይበት የነበረው ችግር በፓርቲያችን በብልፅግና ፓርቲ መሪነት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት አምስት አመታት በርካታ ውስብስብ አገራዊ ችግሮችን በመፍታት ለዜጎች የምትመችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል። በተለይም ሲጎተት የነበሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተቻለበት ጊዜ ላይ ተደርሷል። አሁን የተመዘገበው ውጤት ለአገራችን ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ፈተናዎችን ተጋፍጦ በማሸነፍ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የፓርቲው ቁርጠኝነቱ አሁን የታዩ ስኬቶች ማሳያ ናቸው።
በአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት!
በአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ ምን እየተሰራ ነው:-
#ከቃል_እስከ_ባህል
#from_pledge_to_practice
#waadaa_hanga_aadeffannaatti
#aa_6month_report
#aa_prosperity
#kolfe_prosperity
#kolfe_woreda_07_prosperity
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ተጠናቀቀ ::
ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ተጠናቀቀ፡፡
"ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የተጠናቀቀው ባለሥምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው፡፡
ጉባዔው ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህ በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲያገለግሉ በድጋሚ የመረጠው ፓርቲው ፥ ሕዝቡን ያሳተፉ ዘርፈ-ብዙ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ያረጋገጠው፡፡
ፓርቲው የሚዲያ ነጻነት እንዲጠበቅ እንደሚሠራ እንዲሁም አፍራሽ ተልዕኮን ያነገቡ አካላትን አበክሮ እንደሚታገል የጉባዔውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቀረበው የአቋም መግለጫ ላይ አስገንዝቧል፡፡
የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተመላከተው፡፡
ሁልጊዜም ለሠላም ቅድሚያ በመስጠት፤ ግጭትን ለማስቀረት ሁሉም የፓርቲው አመራር እና አባላት በትጋት እንዲሠሩ አቅጣጫ መቀመጡ በአቋም መግለጫው ተገልጿል፡፡
ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።
ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ክቡር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧቸዋል። ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
በተያያዘ ዜና ጉባኤው ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና ክቡር አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧል።
ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
በገዢ ትርክት እና በሌብነትና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በገዢ ትርክት እና በሌብነትና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ለብልፅግና ቤተሰብ አባላት ስልጠና ተሰጠ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ወረዳ 07 ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ ገዢ ትርክታችንን ለብሔራዊ ጥቅም በማዋል ከምን ጊዜውም በላይ በትኩረት እና በእውቀት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ገዢ ትርክታችንን ማስረፅ ይገባናል በማለት ለሀገረ-መንግስት ግንባት ብልፅግናችንን ለማስፈን የስልጠና መድረክ ማዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
በገዢ ትርክት ዙሪያ ስልጠናውን የሰጡት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ አደም መሀመድ ፓርቲያችን ብልፅግና ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትን እና ህብረብሔራዊነትን የሚያጎለብት የብሔራዊነትና የአርበኝነት ክብርን የሚያጎናፅፍ አሰባሳቢውንና ታላቁን አገራዊ ትርክት ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሯል። ትርክትን የምንገራው ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የመከባበር እሴቶቻችንን በማጎልበት ነው ብለዋል። በመጨረሻም በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 07 ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ስራ ሂደት አቶ ገ/ወልድ ሰተቶ በሌብነትና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ሰልጠና በመስጠት ከታሳታፊዎችም ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶበት ስልጠና ተጠናቋል።
በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ እና የብልፅግና ምክር ቤት አባል በመሆን ለተመረጡት የከተማችን አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ እና የብልፅግና ምክር ቤት አባል በመሆን ለተመረጡት የከተማችን አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
የብልፅግና ፓርቲ ም/ቤት ስራ አስፈፃሚ አባላት ሆነው የተመረጡት:-
1. ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ደሳ
2. ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ሲሆኑ፥
የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል በመሆን የተመረጡት ደግሞ:-
1. ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ
2. ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ
3. ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ
4. ኢ/ር ወንድሙ ሴታ
5. ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር
6. ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ
7. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ
8. ዶ/ር ሂሩት ካሳው
9. ክብርት ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም ምኞቱን እየገለፀ ፣ መጪው የስራ ጊዜ ለሁሉም ተመራጮች ብሩህ እንድሆንላቸው ይመኛል።
በቃል የሚፀና ባህል፣ ለኢትዮጵያ ልዕልና!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፍራንስ ውይይት የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት በተገኙበት ስኬቶችን ለማስቀጠል ብሎም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ጊዜያት ለማረም በሚያስችል በወረዳ ደረጃ ቅድመ ኮንፍረንስ በደመቀ መልኩ ተካሄደ።
አቶ ለማ ቱሉ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ ዐ7 ዋና ስራ አስፈፃሚ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት በማስተላለፍ ብልጽግና ፓርቲ ለህብረተሰቡ ቃል የገባውን በተግባር በመፈጸም ለትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ የህዝብ ቅርስና ሀብት የሆኑ፣ ለቱሪዝም መስህብ ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ጀምሮ በመጨረስ ባህል ያሳየና ያረጋገጠ፣ ሰው ተኮር ስራዎች አስፍቶ በመስራት፣ የአረንጓዴ አሻራ ግሪን ሌጋሲ በማስቀጠልና ባህል በማድረግ እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፍ ላይ የተማሪዎች ምገባና የቁሳቁስ አቅርቦት በማመቻቸት፣ የውስጥና የውጪ ዲፕሎማሲ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የተቋማት ሪፎርም በመስራት የተገልጋይ እርካታ በማሳደግና ጠንካራ ተቋማት በመገንባት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም የሰላምና ፀጥታ ስራ በትኩረት በመስራት ሰላም መረጋገጡና የሀገር ኢኮኖሚ በማሳደግ ትልቅ ስራ መሰራቱና ገልጸዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ በበኩላቸው በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እና መመሪያዎች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ሰነድ በማቅረብ "ከቃል እስከ ባህል!" በሚል መሪ ቃል 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፍራንስ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመጀመርያው የፓርቲው ጉባኤ ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ኢትዮጵያን በልዕልና ጎዳና በማስቀጠል ውጤታማ ተግባር የፈፀመ እና የማስፈፀም በዋናነት የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነትን በመፍጠር ስኬታማ ስራዎችን በውጤት ማከናወን የቻለ ሲሆን ፥ የነበሩ ስኬቶችን ለቀጣይ አቅም እንዲሆኑ ለማድረግ እና የነበሩ ጉለቶችን ለቅመው የጋራ ተግባቦት በመፍጠር በቁጭት እና በትኩረት ለመስራት የሚያግዝ የሚያሳድግ፣ ተደማሪ አቅምና አስተሳሰብ ያጎለብታል በማለት ገልፀዋል።
ባለፉት 6 ወራት በፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የተሰሩ ሰዉ ተኮር ተግባራት፤የልማት አበይት ስራዎችንና በብራንዲንግ ሥራ የተከናወኑ ተግባራትን የሚያሳይ የፎቶ ስብስብ ለምልከታ ቀርበው በብልፅግና ፓርቲ አባላት፣ በወረዳዉ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ ባለጉዳዮችና ነዋሪዎች የፎቶ መስኮት አውደርዕዩን ጎብኝተዋል፡፡
የተሰሩ ስራዎችን ከሚዲያ ባሻገር በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች በመጠቀም ስራዎችን እና መረጃዎችን ተደራሽ የተደረገበት ሁኔታና ብልፅግና ፓርቲ እያከናወነ ያለው ተግባራት ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ጎብኝዎች አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
የመንግሥት እና የፓርቲ ውስጠ ሥራዎች ተገመገመ ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር ሁሉም የወረዳ አመራሮች በተገኙበት የመንግሥት እና የፓርቲ ውስጠ ሥራዎች ተገመገመ ።
በሁሉም ብሎኮች ላይ በሌማት ትሩፋት የሚሰሩ ስራዎች በእጽዋት እና በእንስሳት ዘርፎች ላይ ነባሩ በማስቀጠል አዳዲሶቹ ወደ ተግባር በማስገባት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምርት እና ምርታማነት በማሳደግ የኑሮ ውድነት ማረጋጋት እንደሚገባ በመግለፅ የፓርቲ ስራዎች የሁላችንም ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ አባል በህዋስ ውይይት ላይ በመገኘት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ብልሹ አሰራርን በመታገል የፓርቲውን እሳቤ ማስረፅ እንደሚገባ የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ወንድሙ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ባህልን በማፅናት ብልፅግናችንን እውን እናድርግ!
ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ተፈጥሯዊ ፀጋዎቿን እና ሰው ሰራሽ ሀብቶቿን አቀናጅቶ መምራት ባለመቻሉ ሀገራችን በድህነት አረንቋ ውስጥ ቆይታለች፡፡ ከድህነት ለመላቀቅ የሚደረገው ጥረትም ያልተቀናጀና ውስንነት የበዛበት ነበር፡፡ ለአብነትም ከዛም ከዚህም የመሰረተ ድንጋይ ሲቀመጥላቸው የቆዩ ፕሮጀክቶች አስታዋሽ አጥተው የህዝባችን የመልካም አስተዳደር ችግር ምንጭ ሲሆኑ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይን በመሰነቅ የአሰራር ማነቆዎችን ከስር መሰረቱ በመቅረፍ፣ አዲስ የስራ ባህልን በመገንባት እየተደረገ በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ፕሮጀክቶችን በመፍጠርና በመፍጠን የመጨረስ ባህልን ማዳበር ተችሏል፡፡
ብልፅግና አይደፈሩም አይቻሉም የተባሉትን ትልልቅ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ እና ለረጅም ጊዜ ሳይጠናቀቁ የቆዩትን አሰራራቸውን በመፈተሽ በማስተካከል ለፍፃሜ በማብቃት ቃሉን በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በነበሩ ብልሹ አሰራሮች ወደ መቆም ተቃርቦ የነበረ ሲሆን ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ በተከናወነው ስኬታማ ሪፎርም ግድቡን በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡
በንግግር ደረጃ ጭምር እንዳይነሳ ሆኖ የቆየውን የባህር በር ጉዳይ ፓርቲያችን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የሀገር ህልውና ጉዳይ አድርጎ በመያዝ ሀገራዊ ታሪካዊ ስብራቶችንም መጠገኑን አጠናክሯል፡፡ሀገራችን የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የሌሎችንም ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀምን በማዳበር ሳይንስ ሙዝየምን የመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ሲሆን ከዘመኑ ጋር አብሮ ለመራመድም ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በኢትዮጵያ እየተሰሩ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የቱሪስት መስዕብ፣ የገቢ ምንጭ በመሆናቸው ብልጽግና የስራ ባህል እና የአጨራረስ ብቃት የሚያረጋግጡ እና የሁለንተናዊ ብልፅግናችን ጉዞ ስኬት ናቸው። ከአንድነት ፓርክ ጀምሮ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሃገር እና በገበታ ለትውልድ ደግሞ ጎርጎራን፣ ሃሌላ ኬላን፣ ወንጪን፣ ቤኑን እንዲሁም ሌሎችን ባልተገመተ ፍጥነት ባልተለመደ ጥራት በመጨረስ የመንግስታችን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ጎልቶ ታይቷል፡፡
በከተማችን እና በሀገራችን የመጀመሪያ የሆኑ ግዙፍ የእንጀራ ፋብሪካዎች፣ ሸማቹንና አምራቹን በቀጥታ በማገናኘት ህገ ወጥ የገበያ ሰንሰለቱን ያሳጠሩ ግዙፍ የግብርና ምርቶች መገበያያ ማዕከላት ፣ በውስብስብ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን የከተማችን ሴቶች ተስፋ ያለመለመና ተጨባጭ ለውጥ እያጎናፀፈ የሚገኘው የነገዋ የሴቶች የተሀድሶና የልህቀት ማዕከል እና ሌሎችም ግዙፍ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ያመላከቱ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባን ስም እና ግብር በማገናኘት እንደ ስሟ ውብ የሆነች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ ለመገንባት የተጀመረው የኮሪደር ልማትም በታቀደለት አግባብ በ7/24 የስራ መርህ እየተመራ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ የከተማችንን ነዋሪ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አቃሏል፡፡ የከተማችንንም ገፅታ በእጅጉ የቀየረው ይህ ፕሮጀክት ለበርካታ ሴቶች እና ወጣቶችም የስራ እድል መፍጠር አስችሏል፡፡ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፍቶ እየተተገበረ ሲሆን ከመጀመሪያው ተሞክሮዎችን በመቀመር በመልካም አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡
በፓርቲያችን የጠራ እሳቤ በመንግስታችን አዳጊ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኘው ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዟችን ታላላቅ ፕሮጀክቶችንም ለህዝባችን በማበርከት ዕድገታችንንም ይበልጥ ያፋጥናል፡፡
ትብብርና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለጋራ ተጠቃሚነት እና ለዘላቂ አብሮነት !
አስቦና አልሞ የሚጀምረው የመደመር ትውልድ በጥራት እየፈፀመ ቃሉን አፅንቷል፡፡ የኢትዮጵያን ልዕልና በማብሰር የንጋት ዘመንን በብርሃናማ ጉዞ ለማፅናት በወል እየተጋን ለሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን እየገነባን ነው። ዘመንን በዋጀ አርበኝነት በተደማሪ አቅም ተምሳሌታዊ ብልጽግና የሆነች ሀገርን እውን ለማደርግ ያሉንን ዕምቅ ዓቅሞችና ፀጋዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የጠሩ እሳቤዎቻችንን አልቆ መፈፀምና አሰባሳቢ ትርክትን ማስረፅ ተገቢ ነው። ፓርቲያችን ነገን ታሳቢ አድርጎ በጥልቅ ዕሳቤ በጥራትና ትጋት ፈጽሞ ሀገራዊ ልዕልናን በማብሰር ምንዳን ያሻግራል። የከተማችንን ሁለንተናዊ ተምሳሌትነት በማፅናት የመሻገር ዘመን አብነት፣ የሀገራዊ ልዕልና ግንባታ ማሳያ ሆና እንድትቀጥል የፓርቲያችንን ቃል በተግባር የማፅናት ምዕራፍ እያረጋገጡ መጓዝ ይገባል። ጎረቤትን ያስቀደመና ሀገራዊ ክብርና ጥቅምን ያስጠበቀ በመደመር መርህ የተቃኘ የውጭ ግንኙነት ፖሊስን በመንደፍም ከምንጊዜው በላይ ውጤታማ ተግባር እየተሰራ ይገኛል። ከሀገራት ጋር ወንድማማችነትን ያማከለ የጋራ ተጠቃሚነትና ፍትሃዊነትን ሚዛን የጠበቀ ግንኙነታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ብልጽግና የአፍሪካ የከፍታና ልዕልና ተምሳሌት የሆነች ለጎረቤት ሀገር ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካዊያንም አቅም የምትሆን ሀገር ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። በጋራ ተጠቃሚነትና ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተው ሀገራዊ የብልጽግና ራዕያችን ለሰላም ዕሴት ግንባታም ብርቱ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ የሰላምንና የአብሮነትን ዋጋ ጠንቅቆ የሚረዳው ፓርቲያችን ሀገራዊ ልዕልናን የመገንባት ህልም ሰንቆ ተጨባጭ የብርሃን ጭላንጭልን ፈንጥቋል።
ኢትዮጵያ በመሪዎቿ ጥበብ፣ በልጆቿ የተባበረ ክንድና ተደማሪ አቅም አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን ዕውን ታደርጋለች። ዘላቂ ሰላምና ጥቅምን ያስከበረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነገን በጽኑ አለት ላይ ለማንበር ወሳኝ ነው። ከዚህ አኳያ ፓርቲያችን ትናንትን፣ ዛሬና ነገን በማስተሳሰር ሀገራዊና ቀጠናዊ ትብብርን በጠበቀ መልኩ ሁለንተናዊ ተምሳሌትነትን ያፀናል።
ሀገር የቅብብሎሽ ድምር ውጤት ነች። ያኔ አባት እናቶቻችን የሰሩት ደማቅ ታሪክ ለዛሬ ኩራት፣ ስንቅና ምንዳችን ነው። ዛሬ የምናሳርፈው አሻራ ለነገ የትውልድ ውርስ መስፈንጠሪያና መነሻ እርሾ ነው።
ትውልድ በቸካይና ጎታች በሆነ አስተሳሰብ አይታሰርም፤ ይልቁን ዘመንን ይዋጃል፣ ዛሬ ዓልሞ ነገን ይገነባል። መደመር የአስተሳሰብ ምጥቀት የወለደው ነባር ዕሴትን ያቀፈ አዳዲስና ዘመንን የዋጁ ዕሴቶችን ያካተተ የትናንትን ከዛሬና ነገ ጋር ያቆራኘ ብልጽግናዊ መንገድ ነው። ለዚህም ነው የመደመር ትውልድ ዛሬን እየተጋ የነገዋን ኢትዮጵያ እየገነባ የሚገኘው።
ብልጽግና ሁለንተናዊ ተምሳሌትነቷ የተረጋገጠ የአፍሪካዊያን ሁሉ ኩራት የሆነች ውብ አዲስ አበባን ለመገንባት ባላሰለሰ ጥረት ከፍተኛ የሆነ ዕምርታን እያሳካ ይገኛል። በመዲናዋ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በጥራትና ፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነው የብዙሃንን ህይወት መቀየር ተችሏል።
ውብና ማራኪ ከተማ ትሆን ዘንድ አጠቃላይ ገፅታዋን በመቀየር የቱሪዝም ፍሰቱን የሚጨምርና የትራፊክ ፍሰቱን የሚያቀላጥፍ የኮሪደር ልማት ሌላው የከተማችን ድምቀት ነው። ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድልን በመፍጠር የነዋሪውን ቀጥተኛ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከጅምሩ ያረጋገጠው ልማታችን ሁለንተናዊ ተምሳሌት የመሆን ግስጋሴን እያሳለጠ ነው።
በህብረ ብሔራዊ አንድነቷ የፀናች፣ በህብር ደምቃ በመደመር የምትተጋ፣ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን የምታበዛ ሀገር ዕውን እየሆነች ነው። ይህ ትውልድ ታሪክን ጠብቆ በእራሱ የወል እውነትን የሚያፀና በብሔራዊ ገዥ ትርክት ዘመንን የሚሻገር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ያረጋግጣል። በዚህ የመደመር የወንድማማችነትና እህትማማችነት የፀና ትጋታችንን በጥራትና ፍጥነት በመጨመር ከፍታችንን እናፀናለን።
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!!
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ቤት
ወይዘሮ ነኢመቱላህ ከበደ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
*******************
በዛሬው እለትም ከቀድሞው የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከአቶ ንጋቱ ዳኛቸው የስራ ርክብክብ አድርገዋል።
ወይዘሮ ነኢመቱላህ ከበደ ከዚህ በፊት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የመሰረተ ልማትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።
መልካም የስራና የስኬት ጊዜ ይሁንልዎ።
Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል:: በዚህም መሰረት:-
1. አቶ ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
3. ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ
5. አቶ ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ
6. አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
7. አቶ ታረቀኝ ገመቹ - የንግድ ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ
መልካም የስራ ዘመን
ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው።
ብልጽግና ፓርቲም ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እንዲሁም እውነት፣ እውቀትና ጥበብን መለያው አድርጎ ባለፉት አምስት ዓመታት ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል። በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችም የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ ናቸው። በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ አዳዲስ ድሎችን በማስመዝገብ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለመገንባት እንሰራለን።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለተተኪ አመራሮች በሚዲያ አጠቃቀም፣ በተቋም ግንባታና በመሪነት ጥበብ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
ኮልፌ ወረዳ 07 ፓርቲ ሚዲያ
ህዳር 20 ቀን 2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አዘጋጅነት በወረዳው ለሚገኙ ተተኪ አመራሮች በሚዲያ አጠቃቀም፣ በተቋም ግንባታና በመሪነት ጥበብ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
ያለንን እውቀት በማሳደግ፣ አቅምን በመጠቀም የፓርቲያችን ራዕይን እውን ለማድረግ ጠንካራ ፓርቲ፣ ለጠንካራ መንግስት፣ ጠንካራ መንግስት ለጠንካራ ሀገር መፍጠር እንደሚገባ የወረዳ 07 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብድልባሲጥ ተማም ገልጸዋል።
የአላማ ጽናት፣ ብቃትና ቁርጠኝነት ለእውነተኛ ተግባር በመፈጸም ስኬታማና ውጤታማነት መሆን እንደሚገባ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ አደም መሐመድ አስገንዝበዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 5ኛ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ የምስረታ በዓል አከባበርን አስመልክቶ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅናና ምስጋና መርሀ -ግብር አካሔደ።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የተመሰረተበትን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማ ደረጃ የማጠቃለያና የእውቅና መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተካሔዷል።
በፓርቲው የምስረታ በዓል ማጠቃለያና የእውቅናና ምስጋና መርሀ -ግብር ላይም ለምስረታ በዓሉ አከባበር አስመልክቶ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የ2017 በጀት ዓመት የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራ ማስፈጸሚያ ሰነድ ዕቅድ ከወረዳው አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ።
ኮልፌ ወረዳ 07 ፓርቲ ሚዲያ
ህዳር 18 ቀን 2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራ ማስፈጸሚያ ሰነድ ዕቅድ ከወረዳው አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ።
አዳዲስ የከተማ ግብርና በማስጀመር ነባር የከተማ ግብርና በማስቀጠል ምርት ምርታማነት ማሳደግ የሌማት ትሩፋት ስራችን በውጤታማነት መፈጸም እንደሚገባ የወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ተሉ ገልጸዋል። አክለውም ሁሉም ነዋሪ በዕቃም ሆነ ባለችው ቦታ ዶሮ በማርባት፣ የጓሮ አትክልት በማልማት እንዲሁም የዳልጋ ከብቶች በማርባት ራስን በምግብ በመቻል ለሌሎችም በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ውድነት ማረጋጋት እንደሚቻል ገልጸዋል።
በ90 ቀን ውስጥ በግቢና በዕቃ የጓሮ አትክልት ለ1,425 ለሚሆኑ አባወራዎች እንዲያመርቱ ማድረግ፣ በጥቅሉ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችና በጓሮ አትክልት ና ፍራፍሬ ምርት ምርታማነት በማሳደግ 1,273 ቶን የሚደርስ ምርት ማምረት እንደሚገባ የወረዳው ከተማ ግብርናና አርሶ አደር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሲሳይ ገ/ወልድ ገልጸዋል።
Heads of Government Ethiopia
Abiy Ahmed Ali (Oromo: Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe (Oromo: Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.[
Latest Post